ከእስልምና ወደ ክርስትና የእምነት ጉዞዬ

Yücel from Turkey

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

የተወለድኩት በቱርክ ሲሆን ሙስሊም እንድሆን ተደርጌ ነው ያደግሁት፡፡ እስልምና እምነቴ፣ ባህሌና መታወቂያዬ ነበር፡፡ የእስልምናንም እውነትነት በተመለከተ ምንም ዓይነት ጥርጥር አድሮብኝ አያውቅም ነበር፡፡ በቁርአንና በመጨረሻውም ነቢይ በሙሉ ልቤ አምን ነበር፡፡

በሕይወቴ ሁሉ ሙስሊም መሆን እፈልግ ነበር ይህም ከሙስሊም ቤተሰብ ውስጥ በመወለዴ ሳይሆን እስልምና ለኔ እውነት ስለሆነ ነበር፡፡ ከዚያም እኔ ስለ ሌሎች ሃይማኖቶች ለማጥናት ወሰንኩኝ፡፡ እኔም ሌሎች ሰዎች በእስልምና ለምን እንደማያምኑ እደነቅ ነበር፡፡ ስለዚህም በሌሎች ሃይማኖቶች የሚያምኑ ሰዎችን (በመደነቅ) እመለከት ነበር፡፡

ቁርአንን አነባለሁ፣ እናም ክርስትያኖች ኢየሱስን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ስላደረጉት ብቻ ገሃነም ይሄዳሉ የሚለውን ሳነብ ተደነቅሁኝ! (ለምሳሌም ያህል 5.72 ቁርአንን አንብቡ እንደሚከተለው ይላል፡- ‹እነዚያም አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው፤ ያሉ በእርግጥ ካዱ፣ አልመሲሕም አለ፡- የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታቸሁን አላህን ተገዙ እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ መኖሪያውም እሳት ናት ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡›   ይህንንም ክፍል ልረዳው አልቻልኩም፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ሃይማኖት አይደለምን? እግዚአብሔር ኢየሱስን አልላከውምን? ምንም ጥቅም የሌለው የመሰለውንና ሊያስተምር ያልቻለውን ነቢይ ኢየሱስን እግዚአብሔር ለምን ላከው?

ኢየሱስ እንደ ነቢይ ተልእኮውን ሊያሳካ አልቻለም ሰዎች እሱን እግዚአብሔር በማለት ጠርተውት አልተረዱትም፣ ደግሞም በስተመጨረሻው እግዚአብሔር ከመሰቀል እሱን ማዳን ነበረበት፡፡ ስለዚህም እግዚብሔር ኢየሱስን ለምን ላከው?

ስለዚህም ስለክርስትያን ጓደኞቼ (ሳስብ) እጅግ በጣም አዝናለሁ፡፡ እኔም ስለ ክርስትና ብዙ ተጨማሪ ነገሮችን ተምሬ እና አውቄ ክርስትያን ጓደኞቼን ለመርዳት አሰብኩኝ፡፡

አዲስ ኪዳንንም ገዛሁኝና ማንበብን ጀመርኩኝ፡፡ እውነተኛውም ዓላማዬ ስህተትን ለመፈለግ ነበር፡፡ እንዲያውም ከመጀመሪያው አልጀመርኩኝም፡፡ ከመልእክቶች ውስጥ አንዳንድ ምዕራፎችን ማንበብን ጀመርኩኝ፡፡ እያነበብኩኝም እያለ ባገባችሁ ጊዜ የእናንተ አካል የትዳር ጓደኛችሁ ነው እና የእሱ ወይንም የእሷም አካል የአንተ/የአንቺ ነው የሚለውን ሐሳብ በእውነት በጣም ወደድኩት፡፡ እኔም አዲስ ኪዳን ለሴቶች ትልቅ ጠቀሜታንና ስፍራን እንደሚሰጣቸውም ተመለከትሁ (ማለትም አዲስ ኪዳን ሴቶችን ሁለተኛ ደረጃ ዜጋዎች አያደርጋቸውም)፡፡ ከዚያም ስህተትን ላላገኝ እችላለሁ ብዬም ተገነዝብሁና በክርስትና እምነት በጣም ዝንባሌ አደረብኝ፡፡ ስለዚህም ያንን መጽሐፍን ማንበብን አቆምኩኝ፡፡

አንድ ቀንም በጣም ጥሩ ጓደኛዬ ስለ ክርስቶስ የሚያወራ የክርስትያን ጓደኛ እንዳለው ነገረኝ፡፡ የስልክ ቁጥሩንም ጠየቅሁትና ደወልኩለት፡፡ እሱም በቤተክርስትያን የሚደረግ የክርስትያኖች ስብሰባ ላይ እንድገኝ ጋበዘኝ፡፡ እዚያም ሄጄ የቱርክ ክርስትያኖች በዚያ ስብሰባ ላይ መኖራቸውን አየሁኝ፡፡ ይህንንም ሳይ ላምነው አልቻልኩም ምክንያቱም ስለ እስልምና በቀላሉ ትምህርት በሚያገኙበት አገር በቱርክ ውስጥ እያሉ እንዴት ቱርኮች ክርስትያን ይሆናሉ? እኔም እነዚህ ክርስትያን ቱርኮች በማህበራዊ ሕይወታቸው ደካሞች የሆኑና በራሳቸው መኖር ስለማይችሉ በእንደዚህ ዓይነት እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተዋል ብዬ አሰብኩኝ፡፡

ይሁን እንጂ ወደዚህ ስብሰባ መሄዴን ተደሰትኩበት ምክንያቱም ጥያቄ መጠየቅንና ስለ ሃይማኖት ውይይት ማድረግን እችል ነበርና፡፡ በሁለተኛውም ሳምንት እኔም በጣም ጥሩ ጓደኞዬን ወደ ስብሰባው ጋበዝኩት፡፡  

አንድ ቀን ይህ ክርስትያን ጓደኛችን እኔንና በጣም ጓደኛዬን እቤቱ ሄደን የኢየሱስ ፊልም የተባለን ፊልም እንድንመለከት ጋበዘን፡፡ በፊልሙም ውስጥ ኢየሱስ ‹ከእኔ በኋላ ነቢይ ይመጣል በእሱ እመኑ› ብሎ ይናገራል ብዬ እጠባበቅ ነበር፡፡ ያስደንቃል ያንን ነገር እሱ አላለውም ነበር፡፡

ስለዚህም አሁን እየተረዳሁት ያለው ክርስትና እኔ ከማውቀው ክርስትና የተለየ መሆኑን ተገነዘብሁ፡፡ በዚህ ጊዜም እንደገና አዲስ ኪዳንን ማንበቤን ጀመርኩኝ፡፡ አዲስ ኪዳንንም እያነነብኩ እያለሁ መሐመድን ወይንም ኢየሱስን ከሁለት አንዱን ማመን እንዳለብኝ ተረዳሁ፡፡ ኢየሱስ እሱ ብቸኛው መንገድ እንደሆነ ነው የተናገረው መሐመድ ግን የመጨረሻው ነቢይ እንደሆነ ነው የተናገረው፡፡

‹ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም› ዮሐንስ 14.6::

ከዚያም አንዱን ጓደኛዬን ስለ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ላይ የተተነበየ ትንቢትን ሊያሳየኝ ይችል እንደሆነ ጠየቅሁት፡፡ እሱም የጥቅሶችን ዝርዝር ሰጠኝ እነዚያንም ጥቅሶች ከብሉይ ኪዳን ውስጥ አነበብኳቸው፡፡ ኢሳያስ 53፣ መዝሙር 22፣ መዝሙር 2 እና ሌሎችንም ብዙዎችን ጨምሮ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ስለሚመጣው መሢህና፣ ስለ ኢየሱስ እና ስለ ስቅለቱ የሚናገሩ ናቸው፡፡

በዚህ ነጥብ ላይ ቀደም ብዬ ኢየሱስ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት መሆኑን አይቻለሁኝ፡፡ ይሁን እንጂ የዘላለም ስህተት እንዳልሰራ ደግሞ ፈራሁኝ፡፡ ከዚያም መንገዱን አገኘሁት …

ሰዎች በተለያየ ሃይማኖት ያምናሉ እነዚህ ሁሉ ሃይማኖቶች ሁሉም ትክክል ሊሆኑ አይችሉም፡፡ እግዚአብሔርንም ለማግኘት የአዕምሮ እውቀት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ወደ እግዚአብሔር ብፀልይና ነገሩን ሁሉ ለእሱ አሳልፌ ብሰጠው ከዚህ በኋላ ልጨነቅበት አልችልም በማለትም አሰብኩኝ፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ስህተትን ሊያደርጉ እንደሚችሉ፣ እግዚአብሔር ግን እንደማይሳሳት ስለማምን ነው፡፡ ፀሎቴም የሚከተለውን ይመስል ነበር፡ ‹እግዚአብሔር ሆይ ላውቅህ እፈልጋለሁ ላገለግልህ እፈልጋለሁ እኔም የገነትን ደስታ አይደለም የምፈልገው ወይንም በሰዎች መካከል የሃይማኖተኝነት ክብርንም አልፈልግም ነገር ግን እኔ አንተን ለማወቅ ብቻ ነው የምፈለግው፣፡፡ ስህተቶችን ለመስራት አልፈልግም፡፡ ስለዚህም እኔ አንተ እግዚአብሔር መሆንህን እንዳውቅ እባክህን እራስህን ግለጥልኝ› የሚል ነበር፡፡

ይህን ፀሎት በፀለይኩኝ በነዚያ ሳምንታት ውስጥ፣ በሕይወቴ ውስጥ ልዩ የሆነን ልምምድ አየሁኝ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ስገልጥ የፀሎቴ መልስ የሆነው ነገር እዚያ በዓይኖቼ ፊት ተደቀነብኝ፡፡

ኢየሱስን መከተል የሚገባኝ መሆኑን ለማወቅ ከእግዚአብሔር ዘንድ ብዙ ምልክቶችን ጠይቄ ነበር፡፡ እሱም እነዚያን የጠየቅኳቸውን ምልክቶች ሁልጊዜ አሳይቶኛል፡፡

ከዚያም በ1994 ዓ.ም ኢየሱስን ለመከተል ወሰንኩኝ፡፡ ከዚያንም ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በእሱ ላይ ያለኝን እምነት እያሳደገው ነው፡፡

እናንተስ በእርግጥ እግዚአብሔርን ለማወቅ ትፈልጋላችሁን? ልባችሁን ለእውነቱ ክፈቱ፣ ፀልዩ እና መልስን ከእግዚአብሔር ጠብቁ፡፡

ዩሱል 

 

የትርጉም ምንጭ: My Faith Journey from Islam into Christianity

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ