በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ የሚባሉ ቅራኔዎች
‹ወደ ፍርድም አስቀድሞ የገባ ፃድቅ ይመስላል፣ ባላጋራው መጥቶ እስኪመረምረው ድረስ› ምሳሌ 18.17
የቅራኔዎች መኖር ውንጀላ
በ Jay Smith, Alex Chowdhry, Toby Jepson, James Schaeffer
[ክፍል አንድ] [ክፍል ሁለት] [ክፍል ሦስት] ክፍል አራት [ክፍል አምስት]
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ
ጥያቄ አስራ ሦስት: በ1 ነገስት 15.33 መሰረት የእስራኤል ንጉስ የሞተው በይሁዳ ንጉስ አሳ ሃያ ስድስተኛ ዓመት ነበርን ወይንስ በ2 ዜና 16.1 መሰረት እስከ አሳ 36ኛ ዓመት ድረስ በሕይወት ኖሮ ነበር?
ጥቅሶቹ ሙሉ ለሙሉ፡ “በ1ነገስት 15.33 ላይ ‘በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በእስራኤል ሁሉ ላይ በቴርሳ ንጉሥ ሆኖ ሀያ አራት ዓመት ነገሠ። በ2 ዜና 16.1 ላይ ደግሞ “አሳ በነገሠ በሠላሳ ስድስተኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ ወጣ፥ ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ አሳ ማንም መውጣትና መግባት እንዳይችል ራማን ሠራ።”
ለዚህ ችግር ሁለት መፍትሔዎች ይኖራሉ፡፡ ለመጀመርም ያህል ይህን ችግር የተመለከቱ ሊቃውንቶች የንጉሱ አሳ 36ኛ ዓመት መቆጠር ያለበት አስሩ ነገዶች ከይሁዳና ከቤንያሚን ዘንድ ከወጡበት ዘመን ጀምሮ ነው ይላሉ ያም አንዱ አገር ወደ እስራኤልና ይሁዳ ከመከፋፈሉ ጀምሮ ነው ይላሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የምንመለከተው ከሆነ 36ኛው ዓመት የተከፋፈለው መንግስት የአሳ 16ኛ የንጉስነት ዘመን ይሆናል፡፡ ይህም ደግሞ በእስራኤልና በይሁዳ ነገስታት ታሪክ እንዲሁም በጊዜው በነበረ የታሪክ መዝገብም መጽሐፍ የተደገፈ ነው፡፡ እርሱም ይህንን ስምምነት ተከትሎ የተጻፈ ነው፡፡ (አስታውሱ የዚህ ፅንሰ ሐሳብ ሙሉ ገለፃ Archer, page 225-116 ላይ ይገኛል፡፡)
በ Keil and Delitzsch (pp. 366-367) ደግሞ የመረጡት በ2ዜና 16.1 ላይ ያለውን 36 ዓመትን ቁጥር ነው፡፡ እንደዚሁም በ15.19 ላይ ያለው 35 የሚለው ቁጥር በ16 እና በ15 መካከል ያለ የቀጅዎች ስህተት እንደሆነ አድርገው ነው፡፡ ይህ ችግር ደግሞ ከዚህ በላይ ካየናቸው ቁጥር 5 እና 6 ችግሮች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ቁጥሮቹ የተጻፉት በዕብራይስጥ የፊደሎች ቅደም ተከተል መሰረት ነው (ይህም ከግብፃውያኑ ብዙ ቀጥር ያሉ መስመሮች በኤሌፋንታይን ወረቀቶች ላይ ከተገኙት ይልቅ ነው በቁጥር 5 እና 6 ላይ ከተጠቀሱት ይልቅ ነው)፡፡
ስለዚህም 16 የሚለው ቁጥር በቀላሉ ከ36 ጋር ተምታትቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ እስከ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ 10 ቁጥርን ትወክል የነበረችው (ዮጣ) የምትባለው ፊደል 30 ቁጥርን ከምትወክለው ፊደል (ላሜድ) ጋር እጅግ በጣም ትመሳሰል ነበርና ነው ይህም ሁለት ጥቃቅን ጭረቶች ከዋናው ቀጥ ያለው መስመር በስተግራ በኩል በ30 ላይ ከመያያዛቸው በስተቀር ነው፡፡ ስለዚህም ከአጠቃቀም ብዛት የተነሳ በጥራዞቹ ላይ ከሚኖር አጠቃቀም የተነሳ በጣም ትንሽ ጭረት ነገር (ዮጣ)ን ወደ ላሜድ መምሰል ሊቀይረው ይችል ነበር፡፡ ስለዚህም እንዲህ ዓይነት ነገር በቀደሙት አንቀፆች ላይ ሊሆን የሚችል ነገር ነበር፣ በ2 ዜና 15.19 (በእርሱም ውስጥ ከመጀመሪያው 15 ላይ በስህተት 35 ተብሎ ከተገለበጠበት ላይ) ከዚያም ከ16.1 ጋር ተስማሚ (ወጥ) ለማድረግ ያው አንዱ ጸሐፍት (ወይንም ምናልባትም በቆዩት ጊዜ የጻፈው የወሰነው ውሳኔ 16 ለ 36 በስህተት የተጻፈ መሆኑን ነበር፣ ስለዚህም በእራሱ ቅጅ ላይ ለውጦ አስቀምጦታል ማለት ነው፡፡
ጥያቄ አስራ አራት፡ ንጉሱ ሰለሞን ለግንባታ ስራው ተቆጣጣሪነት የሾማቸው ሰዎች ቁጥር 3 600 (2ዜና 2.2) ወይንስ 3 300 (1ነገስት 5.16) ነበር?
ሙሉ ጥቅሶቹ፡ እንደሚከተሉት ናቸው፡ በ2ዜና 2.2፤ “ሰሎሞንም የሚሸከሙትን ሰባ ሺህ፥ ከተራሮችም የሚጠርቡትን ሰማኒያ ሺህ፥ በእነርሱም ላይ የተሾሙትን ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች ቈጠረ።” የ ነገስቱ ደግሞ 1ነገስት 5.16፤ “ይኸውም በሠራተኛው ሕዝብ ላይ ከተሾሙት ከሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች ሌላ ነው።” (የ1879 እትም ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ይላል)፡፡
ይህ ትልቅ ችግር አይደለም፡፡ ለዚህም በጣም የሚያስኬደው መፍትሄ ማንኛውንም የመቆጣጠር ስራ እንዲሰሩ በተጠባባቂነት የተመረጡትን የተጨማሪ 300 ሰዎችን ቁጥር የዜና መዋዕል ጸሐፊ ጨምሯል ማለት ነው፡፡ የ1ነገስት 5.16 ጸሐፊ ግን ያስቀመጠው ከተጠባባቂዎቹ ውጭ የሆኑትን የሰው ሃይላት ብቻ ነበር፡፡ 3 300 ከሆኑ ቡድኖች ውስጥ ያለምንም ጥርጥር ህመምና ሞት ሊኖር እንደሚችል ግልፅ ነው፣ ይህም እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠሩ ከሚችሉ ተጠባባቂዎች ጭምር ነበር፡፡
ጥያቄ አስራ አምስት፡ ንጉሱ ሰለሞን የገነባው መታጠቢያ ይይዝ የነበረው የውሃ መጠን 2 000 (በ1 ነገስት 7.26) መስፈሪያ ወይንስ 3 000 (በ2ዜና 4.5 መሠረት) መስፈሪያ ነበር?
ሙሉ ጥቅሶቹ፡ 1ነገስት 7.26 “ውፍረቱም አንድ ጋት ነበረ፤ ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር ተሠርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበባዎች ሆኖ ተከርክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር።” 2ዜና 4.5 “ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከንፈሩም አንደ ጽዋ ከንፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም የባዶስ መሥፈሪያ ይይዝ ነበር።”
በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያለው “ይይዝ” ነበር እንዲሁም “መያዝ” የሚለው ይህ በዕብራይስጥ ግስ ሲሆን በእንግሊዝኛው “ይቀበላል” ተብሎ ቢተረጎምም በአማርኛው በትክክል ተላልፏል፣ ትርጉሙም ባህሩ 2000 የባዶስ መስፈሪያ ይዟል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በጣም በሚሞላበት ጊዜ ደግሞ የመጨረሻው የሚይዘው መጠን 3000 የባዶስ መስፈሪያ ያህል ይሆናል፡፡ ስለዚህም የዜናው ጸሐፊ በቀላሉ የዘገበው ነገር አንድ ባህርን የሚፈስ ምንጭ ያስመሰለውን ውሃ እንጂ እንደረጋ ኩሬ ያስመሰለውን የውሃ መጠን አይደለም፡፡ ይህ የሚናገረን ለእኛ በመጠነኛ ሁኔታ ሲሞላ 2000 የባዶስ መስፈሪያ ውሃ ይይዛል ተብሎ የነበረው በጣም ሲሞላ ግን 3000 ባዶስ መስረፊያ የሚይዘው እንደሆነ ነው፡፡
ለዚህ ጥያቄ ሌላው መፍትሄ የሚሆነው ከዚህ በፊት በተጻፈው ውስጥ እንደተነገረው ነው፣ ያም በዕብራይስጥ 2000 ለመጻፍ የሚያገለግሉት ፊደላት በጸሐፍቱ ስህተት 3000 በሚያሳይ የፊደላት ጽሑፍ ተተክቷል ማለት ነው፡፡
ሻቢር (በየካቲት 25 1998 ከጄይ ስሚዝ ጋር ባደረገው ክርክር በበርሚንግሃም እንግሊዝ አገር) ይህንን እንደ ቅራኔ ጠቅሶት ነበር፣ እርሱም ሲናገር የጨመረው መዋኛው ቦታ የክበቡ መካከል 10 ክንድ ከሆነ የክበቡ ዙሪያ 30 ክንድ አንቀፁ እንደሚለው ለመሆን አይችልም በማለት (ፓይ የሚያመለክተው የእርሱ ዙሪያ 31.416 ወይንም የክበቡ መካከል 9.549 ዲያሜትር እንዲሆን ነው) በማለት በክብ የስሌት መሰረት ተመስርቶ ነበር፡፡
በመቀጠልም ሻቢር በመሳቅ የስላቅ አስተያየቱ የተናገረው “እንደዚያ ዓይነት መዋኛ አምጡልኝ እኔም እጠመቅበታለሁ በማለት ነበር”፡፡ ነገር ግን ሻቢር ክፍሉን በሚገባ አላነበበውም ወይንም ይሄድ የነበረው ለርካሽ የሚያስቅ የራሱ የመተኪያ ቅንብር ነበር፡፡ ነገር ግን ለምን? ምክንያቱም ክፍሉ የሚለው እርሱም 8 ሴንቲ ሜትር የሚያክል ውፍረት የነበረው እንዲሁም ከንፈሩ እንደ ሊሊ አበባ ቅርፅ የነበረው ነበር ይላልና ነው፡፡ ስለዚህም የሚወስነው ነገር ከየትኛው ቦታ ላይ ተነስታችሁ እናንተ እንደምትለኩት ነው፡፡ ከጫፉ ወይንስ ከስሩ ነው የምትለኩት ከውስጥ ነው ወይንስ ከውጭ የሚለው ሁሉ ነገር የመጨረሻውን መጠን ስሌት ይወስነዋል፡፡ ከሰፊው ቦታ ላይ ነው ወይንስ ከጠባቡ ከየት ተነስታችሁ ነው የምትለኩት የሚለው ሁሉን ነገር ይወስነዋል፡፡ በመሆኑም አንድ በትክክል የሚለካው ሰው ቢኖር የሚያገኘው የተለያየ የዙሪያ መጠንን ይሆናል፡፡
በሌላ አነጋገር የዚያን ዓይነት ትክክለኛ ቅርፅ ለማግኘት የሚጣጣር ሰው ካለ ሻቢር በእርግጥ ሊጠመቅ ይችላል፡፡ (ነገር ግን መጠመቁ ምንም መንፈሳዊ ጠቀሜታ አይኖረውም፣ አንድን ሰው የሚጠቅመው ነገር እውነትን በቅንነት ማወቅና ለዚያም የሚያስፈልገውን መታዘዝ መስጠት ብቻ ነው)
ጥያቄዎች አስራ ስድስት እስከ ሃያ አንድ፡ ከባቢሎን የተመለሱት የእስራኤላውያን ቁጥር ዘገባ ትክክለኛው የተቀመጠው በየትኛው መጽሐፍ ውስጥ ነው? በእዝራ 2.6፣8፣ 12፣ 15፣ 19፣ 28፤ ወይንስ በነህምያ 7.11፣13፣17፣20፣22 ነው?
(ከአስራ ስድስት እስከ ሃያ አንድ ድረስ ያሉት ጥያቄዎች በሙሉ ያተኮሩት ከዚህ በታች ባሉት የሕዝብ ቆጠራዎች ላይ ብቻ ስለሆነ እዚህ ቦታ ላይ ሁሉም እንደ አንድ ጥያቄ ተደርገው ቀርበዋል)
በመሰረቱ የዚህ ዓይነቱ ችግር ታሪካዊ እውነታን በተሳሳተ መንገድ የመረዳት ችግር ነው፡፡
በሁለቱም በእዝራ ምዕራፍ 2ና በነህምያ ምዕራፍ 7 ላይ ሠላሳ ሦስት የሚሆኑ የቤተሰብ ስሞች ዝርዝሮች ተጠቅሰዋል እነዚህም ከባቢሎን ወደ ይሁዳ የተመለሱት የእስራኤላውያን ቤተሰብ ናቸው፡፡ ከእነዚህም 33 ቤተሰቦች ዝርዝር አስራ ዘጠኙ ቤተሰቦች በሁለቱም መጽሐፎች ውስጥ አንድ ዓይነት ሲሆኑ በቀሩት አስራ አራቱ ቤተሰቦች ውስጥ ያሉት የቤተሰብ አባላት ቁጥር ላይ ልዩነትን ያሳያሉ (ምንም እንኳን ሻቢር የጠቀሰው ስድስቱን ብቻ ቢሆንም)፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ በአንድ የቤተሰብ አባል ቁጥር፤ አንድ ደግሞ በአራት የቤተሰብ አባል ቁጥር፤ ሁለቱ ደግሞ በስድስት የቤተሰብ አባል ቁጥር፤ ሁለቱ ሌሎች ደግሞ በዘጠኝ የቤተሰብ አባል ቁጥር፤ ሌላ ደግሞ በአስራ አንድ የቤተሰብ አባል ቁጥር ልዩነት አላቸው ሌሎች ሁለት ደግሞ በአንድ መቶ ሌላ ደግሞ በ201 ሌላአንድ ደግሞ በ105 በተጨማሪም ሌላ ደግሞ በ300 እንዲሁም በጣም ትልቁ ልዩነት ለአስጋድ ልጆች የተሰጠው ቁጥር መጠን ነው ምክንያቱም ልዩነቱ ያለው በ1100 ነውና፡፡ እንግዲህ እነዚህ የቁጥር ልዩነቶች ሁሉ በእዝራ 2 እና በነህምያ 7 መካከል ያሉት ልዩነቶች ናቸው፡፡
ታዲያ እንዴት አድርገን ነው ለእነዚህ በ14 ቤተሰቦች ውስጥ ላሉት ልዩነቶች ምላሽን ልንሰጥ የምችለው? በእርግጥ መጠነኛ ጥናት ላደረገ ሰው መልሱ በጣም ቀላል ነው፡፡ የሙስሊሙ ተከራካሪ ሻቢር በእነዚህ በሁለቱ ዘገባዎች ውስጥ ትንሽ ጥናትን አድርጎ ቢሆን ኖሮ እነዚህን ጥያቄዎች በመጠየቅ ጊዜውን በፍፁም አያቃጥልም ነበር፡፡ በሁለቱም ዘገባዎች ውስጥ አንድ ዓይነትና የሚለያዩ የቁጥር ዘገባዎች መኖራቸው እራሱ ለእርሱም መፍትሔዎችን ሊጠቁሙት ይገባ ነበር (እናንተ አሁን ይህን የምታነቡ ሁሉ ምናልባትም ይህንን መደምደሚያ አሁን ልትመለከቱ እንደምትችሉት ሁሉ ማለት ነው)፡፡
በሁለቱ መጽሐፍት ላይ ስላሉት የዝርዝር ልዩነቶች በተመለከተ በአዕምሯችን መቀመጥ ያለባቸው ሁለት መሰረታዊ ነገሮች እዚህ ላይ ይኖራሉ፡፡ የመጀመሪያው ምናልባትም ምንም እንኳን የቤተሰብ አባላት ስምና ቁጥር በመጀመሪያ ስማቸው የተመዘገበ ቢሆንም ማለትም ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ያቀዱት በዝግጅቱ መካከል አንዳንዶች ሞተው ሊሆን ይችላል ሌሎች ደግሞ በሕመም ወይንም በሌላ ሊሆኑ በሚችሉ እክሎች ምክንያት ከመሄድ ቀርተዋል፡፡ ስለዚህም በመጨረሻ የሄዱት ሰዎች በመጀመሪያ ለመሄድ ያቀዱት አይደሉም ማለት ነው፡፡ ለትምህርት ቤት ጉዞ ዕቅድን የያዘ ማንም የዚህን ዓይነቱን ሁኔታ በትክክል ሊረዳው ይችላል፡፡
ሁለተኛው እና በጣም ጠቃሚውም ነገር ሁለቱ ምዝገባዎች የወሰዷቸው የተለያዩ ሁኔታዎች ናቸው ይህም ሻቢር ምንም ያልተገነዘበው በጣም ጠቃሚ እውነታ ነው፡፡ የእዝራ ምዝገባ ተከናውኖ የነበረው እርሱ እራሱ በባቢሎን በነበረበት ወቅት ነበር (በ450 ከክርስቶስ ልደት በፊት) ይህም ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ ከመደረጉ በፊት ነበር እዝራ 2.1-2፡፡ የነህምያ ምዝገባ ግን የተወሰደው በይሁዳ ነበር (በ445 ከክርስቶስ ልደት በፊት) ይህም የኢየሩሳሌም ግንብ ከተገነባ በኋላ ነበር (ነህምያ 7.4-6)፡፡ በሁለቱ ዝርዝሮች መካከል የነበረው የብዙ ዓመታት ክፍተት (ከ5-10 ዓመታት) ነበር፡፡ እያንዳንዱ ቤተሰብ እንደገና ሲቆጠርም በእርግጥ ከፍተኛ ልዩነቶችን የሚያመጣ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ሞቶች ወይንም ሌሎች ምክንያቶች ለቤተሰቡ ቁጥሮች መለያየት ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉና፡፡
ብዙ ሊቃውንት እንደሚያምኑት ነህምያ የመዘገባቸው ሰዎች በዘሩባቤልና በኢያሱ መሪነት ወደ ኢየሩሳሌም የደረሱትን ነው በ537 ወይንም በ536 ከክርስቶስ ልደት በፊት (ነህምያ 7.7)፡፡ እዝራ በሌላ ጎኑ ደግሞ የተጠቀመው የቀደመውን የስም ዝርዝር ነው ማለትም ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ፍላጎት ያሳዩትንና ተጓዦቹን ለመደባለቅ ወስነው የነበሩትን ነው ይህም ከባቢሎን ለመመለስ በተደረገው በ450 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው፡፡
በእነዚህ ሁለት ዝርዝሮች መካከል ያለው ልዩነት ሌላው የሚጠቁመው ነገር እነዚያ ሰዎች ሐሳቦቻቸውን ለመለወጥ ሌሎች አዳዲስ ምክንያቶች የነበሩ መሆናቸውንም ነበር፡፡ አንዳንዶች ወደ አለመግባባት ገብተው የነበሩ ሊሆን ይችላል ሌሎች ደግሞ በወቅቱ ላለመጓዝ እና ቆይቶ ለመሄድ የንግድ ምክንያት አጋጥሞአቸው ሊሆን ይችላል፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ህመሞችና ሞቶችም ያለምንም ጥርጥር የነበሩ መሆናቸው እርግጠኛ ነገር ነው፣ እንዲሁም ደግሞ በሌሎች ምክንያቶች በባቢሎን እንቆያለን ብለው ከነበሩት መካከል የመጨረሻው ሰዓትም ምልምሎች ተጨምረውም እንደነበረ ደግሞ መገመት ይቻላል፡፡ ስለዚህም ጎሳዎችና የከተማ ቡድኖች በጣም አናሳ በሆነ ቁጥር ነበር የመጡት፡፡ ሌሎቹ በመጨረሻ ሰዓት ለመሄድ የወሰኑት ነበሩ፤ እነርሱ ናቸው ከአንድ እስከ 1100 የቁጥር ልዩነትን ያመጡት፡፡
ስሞቹን ደግሞ በምንመለከትበት ጊዜ የምናገኘው ነገሩ ቢኖር አንዳንድ ስሞች የተመዘገቡት በተለያየ መንገድ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ከነበሩት አይሁዶች መካከል (እንዲሁም በምስራቅ ከሚኖሩት ጋር) አንድ ሰው ስም፣ ማዕረግና የአባት ስም (የቤተሰብ ስም) ይኖረዋል፡፡ ስለዚህም የሐሪፍ ልጆች (በነህምያ 7.24 የተመዘገቡት) በእዝራ 2.18 ላይ የጆራህ ልጆች ተብለው የተጠሩት ናቸው፡፡ እንዲሁም ደግሞ የሲራ ልጆች (ነህምያ 7.47) በእዝራ 2.44 ላይ የሲያሃ ልጆች የተባሉት ናቸው፡፡
እነዚህን ሁሉ መሰረታዊ ነገሮች በጥንቃቄ ለመመልከት በምንነሳበት ጊዜ በእነዚህ ሁለት ቦታዎች ላይ ያሉት የስም ዝርዝሮች ልዩነቶች በምንም ምክንያት እኛን አያስቸግሩንም፡፡ በማንኛውም ትልቅ የሆነ ታሪካዊ የሰዎች ጉዞና ከአገር አገር መሄድ ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ የቁጥር መቀነስና መጨመር ይከሰታልና፡፡
ጥያቄ ሃያ ሁለት፡ እዝራ 2.64 እና ነህምያ 7.66 ሁለቱም በአጠቃላዩ ስብሰባ ላይ የነበሩት ሰዎች ቁጥር 42 360 እንደነበረ ይስማማሉ ነገር ግን አጠቃላዩ ድምር ሲደመር በእዝራ 28 818 ሲሆን ነህምያ ግን 31 089 ይሆናል፤ ይህ ልዩነት የሆነው ለምድነው?
የዚህ ዓይነቱ ስህተት በአመዛኙ የቀጂ ጸሐፊዎች ስህተት ነው የሚሆነው፡፡
ለዚህ የተምታታ ለሚመስል ችግር ሁለት የሚሆኑ መልሶች ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያው ይህ በአመዛኙ ሊሆን የሚችለው የቀጂዎች ጸሐፊዎቹ ስህተት ነው የሚል ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች ትክክለኛው ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ነገር ግን በአንድ ቦታ ላይ በሚተላለፍበት ጊዜ ጸሐፊው በአንድ ዝርዝር ላይ ስህተትን ሰርቷል እናም አጠቃላዩን በሌላው ቦታ ላይ ቀይሮታል ስለዚህም እነርሱ ሁለቱም እንዲስማሙ አድርጓል፡፡ ይህንን በተመለከተ ያለው አስተያየት ቆይቶ የመጣው ጸሐፍት እነዚህን ነገሮች በሚገለብጥበት ጊዜ ሆነ ብሎ አጠቃላዮቹን በዚህ ጊዜ ላሉት የተሰበሰቡት እስራኤላውያን ቁጥር አስቀምጦታል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ቁጥሩ ትልቅ የሆነው ቆይቶ ነውና፡፡
ሌላው ሁኔታ ደግሞ በብሉይ ኪዳኑ ሊቅ በR.K Harrison የተሰጠው ነው እርሱም የሰጠው አስተያየት በአጠቃላይ 42000 የሚለው ቁጥር ምሳሌያዊ ሊሆን ይችላል በማለት ነው ይህም “የ ዘፀዓትን ምሳሌ እና ሌሎች ተመሳሳይ ልማዶችን ተከትሎ ነው፣ ማለትም ትልቅ ቁጥሮች የእግዚአብሔርን ታላቅነት ለማሳየት ስለሚጠቅሙ ነው፣ እርሱ ሕዝቡንን በድል አድራጊነት ነፃ ማውጣቱን ለማሳየት” (Harrison 1970:1142-1143).
እንዲህ ዓይነት ስህተቶች የዘገባውን ታሪካዊነት በፍፁም አይቀይሩትም ምክንያቱም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ላይ ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተፈጠሩትን ስህተቶች ያርማቸዋልና፡፡ (በዚህ ሁኔታ የተደመሩትን አጠቃላይ ቁጥር)፡፡ እጅግ በጣም የታወቀው ተንታኝ ማቴው ሄንሪ አንድ ጊዜ እንደጻፈው፡ “ጥቂት መጽሐፎች ያለስህተት አይጻፉም፣ ነገር ግን ጸሐፊዎች በዚህ የተነሳ አያስወግዷቸውም፤ እንዲሁም በአታሚዎቹ ምክንያት የተፈጠረው ስህተት በጸሐፊው ላይ አይደረግም (የጸሐፊው ነው አይባልም)፡፡ ቅንነት የተሞላ አንባቢ ግን እነርሱን ከዓውዱ በመነሳት ያርማቸዋል ወይንም እነርሱን በሌላ የስራው ክፍል ጋር በማወዳደር ያስተካክላቸዋል”፡፡
ጥያቄ ሃያ ሦስተኛ፡ ሕዝቡን ያጅቡ የነበሩት ዘማሪዎች ስንት ነበሩ? በእዝራ 2.65 ላይ ያሉት 200 ዘማሪዎች ነበሩ ወይንስ በነህምያ ላይ እንደተገለፀው 245 ነበሩ?
ልክ እንደ ጥያቄ 7 ይህም የጸሐፍቱ ስህተት ነው፡፡ በእዝራ ዘገባ ላይ ያለውን ቁጥር ጸሐፊው ሲገለብጥ ቁጥሩን ከ245 ወደ 200 አጠጋግቶት በመጻፉ ብቻ የተከሰተ ልዩነት ነው፡፡
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡
ከአስራ ሦስተኛው ጥያቄ እስከ ሃያ ሦስተኛው ድረስ ያሉት ልዩነቶች ተብለው ለክርክር የሚቀርቡት ነገሮች የተመሰረቱት በቁጥሮች ላይ ነው፡፡ ስለዚህም አንዳንዶች እነዚህ ልዩነቶች ናቸውና መጽሐፍ ቅዱስን ተቀባይነት የለውም ለማለት ይቃጣሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የቁጥር ልዩነቶች መጽሐፍ ቅዱስን እንደ እግዚአብሔር ቃልነት እንዳንቀበለው ሊያደርጉን አይችሉም፡፡ ከዚህ ይልቅ እንዴት ሊከሰቱ ቻሉ ወደሚል ጥያቄ ይመሩንና ሎጂካዊ መልስን እንድናገኝ የሚረዱንና የሚያስችሉን ናቸው፡፡ ከዚህም የተነሳ ልዩነት የመሰሉ ነገሮችን በማፈላለግ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ እንድናውቅ ለሌሎችም ለማሳወቅ እንድንነሳ ከፍተኛ እገዛን ስላደረጉልን ሳናመሰግናቸው አናልፍም፡፡ ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በእግዚአብሔር መንፈስ በተመሩ ሰዎች ስለሆነ ምንም የአስተምህሮ ስህተት የለበትም፡፡
ከዚህ በላይ የቀረቡት የቁጥር ልዩነቶች እንዴት ወይንም ለምን ተከሰቱ ለሚለው ጥያቄ የተሰጠው ሎጂካዊ መልስ አስገራሚም አጥጋቢም ነው፡፡ ዋናው መሰረታዊ ነገር የቁጥሮቹ ልዩነቶች መኖር መጽሐፍ ቅዱስ በክፍሎቹ ውስጥ የሚያተላለፈውን እግዚአብሔራዊ መልእክት በፍፁም ሊያዛባው አይችልም የሚለው ነው፡፡
ሆኖም ግን የዚህ ድረ ገፅ አዘጋጆች ለአንባቢዎች አንድ መሰረታዊ ጥያቄን ለማስቀመጥ ይፈልጋሉ ይህም፡ “መጽሐፍ ቅዱስን ስታነቡ ልዩነቶች ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ በክፍሉ ውስጥ ባለው መልእክት ላይ ስለምን ትኩረት አያደርጉም? ትልቁ ጠቀሜታ የሚገኘው በውስጣቸው ባለው መልእክት ነው፡፡
ታላቁና የተፈራው ቅዱስ እግዚአብሔር በቀደሙት ሰዎች ታሪክ ውስጥ የገባውን ቃል በመፈፀም በሰዎች ታሪክ ውስጥ ስራውን እንደሰራ ሁሉ በዚህም ዘመን ባሉት በመንግስታትም ሆነ በግለሰቦች ታሪክ ውስጥ የሚሰራ አምላክ ነው፡፡ እሱ ድንቅና ታላቅ ነገሮችን ከመስራት የሚከለክለው ምንም ኃይል፣ ምንም ሃይማኖት እና ምንም ዓይነት አካባቢያዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ አይኖርም፡፡
ከዚህም የተነሳ አሁንም ብዙ ሰዎች በወንጌሉ መልእክት ከኃጢአት እስራት ውስጥ ወጥተው ወደ ተባረከው ተስፋ የዘላለም ሕይወት ተስፋ እንዲመጡ ጥሪው ይቀጥላል፡፡ ከኃጢአታቸው እውነተኛ ንስሐ የገቡና በእርሱ የማዳን ስራ ላይ ብቻ የታመኑት አዲስ ሕይወትን፣ አዲስ ተስፋን አግኝተው አዕምሮአቸውና ሕይወታቸው በሰላም ተሞልቷል፡፡
ይህ አስደናቂ እውነት ለእናንተም ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ ለመታመንና አዲስን ሕይወት ለማግኘት በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እንድትመጡ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ፍቅር እናቀርብላችኋለን ጌታ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡
የትርጉም ምንጭ: "101 Cleared-up Contradictions in the Bible"
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ