1. እስልምናን የመተው አስፈላጊነት

1

እስልምናን የመተው አስፈላጊነት

በዚህ ዘመን በዓለም ላይ ለሚገኙ ብዙ ሕዝቦች በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ቢኖር እስልምናን መተው ነው፡፡ አርነት በምርኮ ውስጥ ላሉት የሚለው ይህ መጽሐፍ ይህንን ፍላጎት ለማሟላት በማለም የተዘጋጀ ነው፡፡ ክርስቲያኖች ተፅዕኖ ከሚያሳድረው የእስልምና መንፈስ ነፃ መውጣት ይችሉ ዘንድ የተለያዩ መሳርያዎችን፣ መረጃን እና ጸሎቶችን ያቀርባል፡፡

የዚህ መጽሐፍ ቁልፍ ሐሳብ የእስልምና መንፈሳዊ ኃይል ሸሀዳ እና ዲህማ በመባል በሚታወቁ ሁለት ቃል ኪዳኖች የሚሰራ ነው የሚል ነው፡፡ ሸሀዳ ሙስሊሞችን ዲህማ ደግሞ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን በእስልምና ሕግ ለተደነገጉ ነገሮች እንዲገዙ ያደርጋሉ፡፡

ይህ መጽሐፍ የሚከተሉትን ነጥቦች ያብራራል፡

·      አንድ ሙስሊም የነበረ ነገር ግን ክርስቶስን ለመከተል የወሰነ ሰው በቃል ኪዳን ከታሰረበት ሸሀዳ እና ከግዴታዎቹ እንዴት ነፃ መውጣት እንደሚችል፡፡

·      አንድ ሰው እንደ ክርስቲያን ነፃነቱን መቀዳጀት የሚችለው እና በሸሪኣ ህግ በዲህማ በኩል ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች ላይ ከተጫነው አዋራጅ ከሆነው የበታችነት እንዴት መላቀቅ እንደሚችል፡፡

ክርስቲያኖች እነዚህን ነገሮች በመካድ ከሁለቱም ቃልኪዳኖች ተላቀው ተገቢውን ነፃነታቸውን መቀዳጀት ይችላሉ፡፡ ለዚሁ ዓላማ ተብሎ ከእስልምና ተፅዕኖ መላቀቅ የሚያስችሉ ጸሎቶች - የአርነት ስርኣቶች - ተዘጋጅተዋል፡፡

ሁለቱ ቃል ኪዳኖች

ኢስላም የሚለው የአረብኛ ቃልራስን መስጠትወይንምመገዛትማለት ነው፡፡ የመሐመድ ኃይማኖት ሁለት መገዛቶችን ለዓለም አቅርቧል፡፡ የመጀመርያው እስልምናን ተቀብሎ የተለወጠ ሰው መገዛት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ሙስሊም ያልሆነ ሰው እስልምናን ሳይቀበል ለእስልምና የበላይነት የሚገዛበት ነው፡፡

·      እስልምናን የተቀበለ ሰው ቃል ኪዳን የሙስሊም የእምነት መግለጫ የሆነው ሸሀዳ ነው፡፡ ይህ የአላህን አንድነት፣ የመሐመድን ነቢይነት እና እነዚህ ነጥቦች በውስጣቸው የያዟቸውን ሐሳቦች በተመለከተ የሚደረግ የእምነት መግለጫ ነው፡፡

·      ለእስልምና ፖለቲካዊ የበላይነት ሙስሊም ባልሆነ ሰው የሚደረግ መገዛት ዲህማ ነው፡፡ ይህ የክርስቲያኖችን እና የሌሎች እስልምናን ያልተቀበሉ ነገር ግን በህጎቹ ለመኖር የተገደዱ ሰዎችን ደረጃ የሚወስን የእስልምና ህግ ተቋም ነው፡፡

ሸሀዳን በመናገር ወይንም ደግሞ ዲህማን በመቀበል የሰው ልጆች እንዲገዙለት የሚጠይቀው የእስልምና ፍላጎት መገታት አለበት፡፡

ብዙ ክርስቲያኖች ክርስቶስን መከተል የፈለገ አንድ ሰው እስልምናን የመካዱ አስፈላጊነት እምብዛም ላይታያቸው ይችላል፡፡ ሙስሊም ሆነው የማያውቁ ክርስቲያኖች በእስልምና የበላይነት መንፈሳዊ ተፅዕኖ ስር እንደሚወድቁ እና የዲህማን ስምምነት ለመቃወም ሙስሊም እንዳለመሆናቸው መጠን እስልምና የሚጭንባቸውን ፍርሃት እና የበታችነት በመቋቋም ግላዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባቸው ምናልባት ጥቂቶች ያስተውሉ ይሆናል፡፡

አርነት በምርኮ ውስጥ ላሉት በነዚህ መንታ የጭቆና ቃል ኪዳኖች (ሸሀዳ እና ዲህማ) በስተጀርባ ያሉትን መርሆች አጠር አድርጎ የሚያቀርብ ሲሆን አንባቢያንም ክርስቶስን፣ የሕይወቱን ኃይል እና ለነፃነታችን በመስቀሉ በኩል የሰጠንን መንፈሳዊ በረከቶች እንዲያስቡ ይጋብዛል፡፡ በመጨረሻም አንባቢያንን ክርስቶስ በነርሱ ፈንታ ያስገኘውን አርነት መቀዳጀት የሚያስችሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆች እና ጸሎቶች ቀርበዋል፡፡

ሉአላዊነትን ማስተላለፍ

ብዙ የእስልምና የነገረ መለኮት ምሑራን ስለ ሉአላዊነት ብዙ ነገር ይናገራሉ፡ ሉአላዊነት የአላህ ብቻ ነው በሚለውም ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ ይህንን ሲሉ የሸሪኣ ህግ በሁሉም የፍትህ እና የኃይል መርሆች ላይ የበላይነት ሊኖረው ይገባል ማለታቸው ነው፡፡

የዚህ መጽሐፍ ቁልፍ ነጥብ የክርስቶስ ተከታዮች ሌሎች ዓይነቶችን መንፈሳዊ ሉአላዊነቶች የመካድ መብትና እንዲያውም ግዴታ እንዳለባቸው የሚናገር ነው፡፡

በክርስቲያን መረዳት መሰረት ወደ ክርስቶስ መመለስ ማለት በነፍሳችን ላይ የሚደረጉ ከክርስቶስ ውጪ ያሉትን ሁሉንም መንፈሳዊ የበላይነቶች እውቅና መንፈግ ማለት ነው፡፡ ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ በጻፈው መልዕክቱ ላይ ወደ ክርስቶስ እምነት መምጣትን ከአንድ መንግስት ወደ ሌላው መንግስት መሸጋገር እንደሆነ ይገልጻል፡

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። (ቆላ 113-14)

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው መንፈሳዊ ስልት ከአንዱ ወደ ሌላው መንግስት የሚደረግ የዚህ ለውጥ መርህ ነው፡፡ ክርስቲያን አማኞች እንደ ደህንነታቸው አንዱ ክፍል በክርስቶስ አገዛዝ ስር ወደመሆን መጥተዋል፡፡ ስለዚህምበጨለማው ተፅዕኖስር አይደሉም፡፡ ለአማኞች ከእስልምና እወጃ በተጻራሪ ይህንን የተፈጥሮ መብታቸው የሆነውን አርነት ለመቀዳጀት እና የራሳቸው ለማድረግ ከምን ውስጥ ተለውጠው እንደመጡ እና ወዴት እንደተለወጡ ሊያውቁት ይገባል፡፡ ይህ መጽሐፍ ለአንባቢያን ይህንን ዕውቀት ይሰጣል እንዲሁም አማኞች ይህንን ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ የሚረዱ መሳርያዎችን ያቀርባል፡፡

ሰይፍ መልስ  ሊሆን አይችልም

የእስልምናን እቅድ ለመቋቋም የሚያስችሉ በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ ይህ ፖለቲካዊ እና የመረጃ ልውውጥ፣ ሰብኣዊ መብቶችን ማቀንቀን፣ ትምህርት፣ እና እውነትን ለማስተላለፍ መገናኛ ብዙሃንን መጠቀም ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን ያካትታል፡፡ ለአንዳንድ ማሕበረሰቦች እና ሃገራት ወታደራዊ ምላሽም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ ሊኖር ይችላል፡፡

መሐመድ እምነቱን ወደ ዓለም እንዲያሰራጩ ተከታዮቹን ሲልካቸው ሙስሊም ላልሆኑ ሰዎች ሦስት ምርጫዎችን እንዲሰጡ ነበር ያዘዛቸው፡፡ የመጀመርያው ሸሀዳን በመያዝ ሙስሊም መሆን ነው፣ ሌላው በዲህማ ደንብ ፖለቲካዊ እጅ መስጠት ነው፣ ነገር ግን ሌላው ምርጫ ሰይፍ ነበር፡፡ ለሕይወታቸው እንዲዋጉ፣ እንዲገድሉ እና እንዲገደሉ፡፡ ልክ ቀቲሉ የሚለው የአረብኛ ቃል ይህንን ትግል ለመግለጽ ጥቅም ላይ እንደዋለው ማለት ነው (ቁርአን 929 2190 2193 2217 9111 ይመልከቱ)፡፡

ነገር ግን ጂሃድን መቋቋም በሙስሊሞች እጅ መሸነፍን የማስከተሉ እድል እንዳለ ሆኖ መንፈሳዊ አደገኛነትም አለው፡፡ የአሮጌው ዓለም ክርስቲያኖች የእስልምናን ወረራ ለመከላከል በተነሱበት ዘመን (ትግሉ ከአንድ ሚሊንየም ጊዜ በላይ ፈጅቷል) የኢቤሪያን ባሕረ ሰላጤ መልሶ ለማስለቀቅ ስምንት ክፍለ ዘመናትን ፈጅቷል፡፡ ለውጦች ይመጡ የነበሩትም በልምምድ ሲሆን ሁል ጊዜ በጎ ለውጦች አልነበሩም፡፡ ሳራሰኖች ሮምን ከያዙ ከሰባት ዓመት በኋላ እና አረቦች አንደሉሺያን ከወረሩ እና ከተቆጣጠሩ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ከሆነው በኋላ ነበር ጳጳሱ ሊዮን 853 .. አብያተ ክርስቲያናትንና ከተሞችን  ከአረቦች ሲከላከል የሞተ ሰው መንግስተ ሰማያት እንደሚገባ ያወጁት፡፡ ከሦስት ክፍለ ዘመናት በኋላ ደግሞ ክርስትናን በኃይል ለማስፋፋት ሲሉ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች የኃጢኣታቸውን ይቅርታ እንደሚቀበሉ ጳጳሱ ጆርጅ ሰባተኛ አወጁ፡፡ ይህ በብዙ ደም ማፍሰስ ወደ አዳዲስ ቦታዎች ከተስፋፋው የእስልምና ስነ መለኮት የተኮረጀ የመስቀል ጦረኞችየቅዱስ ጦርነትዶግማየክርስቲያን ጂሃድንፈጥሯል፡፡

ዛሬ ክርስቲያኖችቅዱስ ጦርነትንአይሰብኩም ነገር ግን ብዙ የክርስቲያኑ ዓለም ለእስልምና የስነ መለኮት አጀንዳ ምላሽበክርስቲያን ጂሃድየስህተት አስተምህሮ መያዙ እስልምናን ከመቋቋም በስተጀርባ ስላለው አደጋ ጥሩ ልምድ ተደርጎ መወሰድ አለበት፡፡

የእስልምና የኃይል መሰረት ወታደራዊ ወይንም ፖለቲካዊ አይደለም ነገር ግን መንፈሳዊ ነው፡፡ እስልምና በባሕርያቸው መንፈሳዊ የሆኑትን ነገሮች በሸሪኣ ተቋም ውስጥ በሚገኙት በሸሀዳ እና በዲህማ በኩል ይተገብራቸዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ እስልምናን ለመቋቋም እና ሰዎችን ነፃ ለማውጣት በዚህ ስፍራ ላይ የተሰጡት መሳርያዎች መንፈሳውያን ናቸው፡፡ ወደ አርነት ለመምጣት የመጽሐፍ ቅዱስን የመስቀል ፅንሰ ሐሳብ በመረዳት በክርስቲያን አማኞች ጥቅም ላይ መዋል እንዲችሉ የተቀናበሩ ናቸው፡፡

በሰው ኃይል አይደለም

በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት ስድስት ክፍለ ዘመናትን በመቅደም የተሰጠ ከእስክንድር አገዛዝ ዘመን በኋላ ከሚመጡ መንግስታት ውስጥ ስለሚነሳ መሪ የሚናገር አስደናቂ ትንቢታዊ ራዕይ አለ፡

በመንግሥታቸውም መጨረሻ፥ ኃጢአታቸው በተሞላች ጊዜ፥ እንቈቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ ይነሣል። ኃይሉም ይበረታል፥ ነገር ግን በራሱ ኃይል አይደለም በድንቅም ያጠፋል፥ ያደርግማል፥ ይከናወንማል ኃያላንንና የቅዱሳንን ሕዝብ ያጠፋል። በመታለሉ ተንኰልን በእጁ ያከናውናል በልቡም ይታበያል፥ ታምነውም የሚኖሩትን ብዙዎችን ያጠፋል በአለቆቹም አለቃ ላይ ይቋቋማል ያለ እጅም ይሰበራል። (ዳን 823-25)

ይህ መሪ የእስልምናን የበላይነት አስተሳሰብ፣ ስኬቱን፣ ማታለልን መጠቀሙን፣ የሌሎችን ስልጣኔና ኃብት በመጠቀም ኃይሉን ማጠናከሩን፣ በሐሰተኛ የደህንነት ስሜት ውስጥ ያሉትን ማሸነፉን፣ የክርስቲያን እና የአይሁድ ማህበረሰቦችን ማጥፋቱን ከመሳሰሉት የመሐመድ ውርሶች ጋር የሚመሳሰል ባሕርይ አለው፡፡

ይህ ትንቢት ስለመሐመድ እና ከርሱ ግብረ ገባዊ እና መንፈሳዊ ድሽቀት ስለመነጨው ኃይማኖቱ የሚናገር ይሆንን? ይህ ከሆነ በዚህ ንጉስ ላይ ስለሚገኘው ድል የተሰጠው ተስፋ ይህ ድልበሰው ኃይልእንደማይገኝ የሚናገር ማስጠንቀቂያ አለው፡፡ ይህንን ኃይል ለማሸነፍ አርነት በፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መንገዶች አይገኝም፡፡

ለብዙ ዘመናት ያደረኩት ጥናትና ምርምር እስልምና ሌሎችን የመቆጣጠር መብት እንዳለው ከመናገሩ አኳያ ይህ ማስጠንቀቂ በጣም ትክክል መሆኑን ተገንዝቤአለሁ፡፡ አለኝ የሚለው ኃይል መንፈሳዊ ነው፣ ስለዚህ ውጤታማና ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመቋቋም እና ነፃነታችንን ለማስጠበቅ መፍትሄው መንፈሳዊ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ሌሎች መንገዶች ምናልባት እስላማዊ ቅየጣን ለመቆጣጠር ይጠቅሙ ይሆናል ነገር ግን የችግሩ ምንጭ ጋር ሊደርሱ አይችሉም፡፡

ከእስልምና አዋራጅ የሆኑ ጥንስሶች እስከወዲያኛው ሊያላቅቅ የሚችለው የክርስቶስ ኃይል እና መስቀሉ ብቻ እንደሆኑ ተረድቼአለሁ፡፡ ከዚያ አመኔታ በመነሳት ነው ይህንን መጽሐፍ ልጽፍ የቻልኩት፡፡ ዓላማውም አማኞች የሰዎችን ነፍስ ለመቆጣጠር ከሚጠቀማቸው ከመንታ ስልቶቹ አምልጠው አርነት እንዲያገኙ ማስታጠቅ ነው፡፡

 

የበለጠ ለማወቅ የሚሹ ከሆነ ...

ይህ መጽሐፍ ግልፅ እና ቀጥተኛ እንዲሆን የታለመ ነው፡፡ ስለ እስልምና የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ እና ከዋናዎቹ ምንጮች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱትን መረጃዎች መረጋገጥ ከፈለጉ ለዚህ ሥራ መሰረት የሆነው ጥናት ቀደም ሲል “The Third Choice: Islam, Dhimmitude and Freedom” በሚል ርዕስ በጻፍኩት መጽሐፌ ውስጥ በስፋትና በጥልቀት ይገኛል፡፡ መጽሐፍ በዚህኛው ውስጥ የተነገሩትን ጉዳዮች በተመለከተ ከዋና ምንጮች የተጠቀሱ ማጣቀሻዎች አሉት፡፡