6. መስቀሉ የአርነታችን መንገድ

ምዕ 6

መስቀሉ የአርነታችን መንገድ

መሐመድ ለመስቀል የነበረው ጥላቻ

በመንፈሳዊው ዓለም በመኖራችን ምክንያት መሐመድ መስቀልን መጥላቱ የተገባ አልነበረም፡፡  በትውፊቶች የተዘገበውን አልዋቂዲ እንደሚናገረው ከሆነ፤ መሐመድ ሰው ቤት ሲገባ የመስቀል ምስል ያለበትን ማንኛውንም ነገር  ካገኝ ማጥፋት ይቀናው ነበር[1]፡፡

መሐመድ ለመስቀል ያለው ጥላቻ ሥር ከመስደዱ የተነሳ ኢየሱስ ወደ ምድር በሚመለስበት ጊዜ የሙስሊሞች ነብይ በመሆን መስቀልን ከምድረ ገፅ ያጠፋል፡፡ ክርስትናንም ያስወግዳል ብሏል፡፡

አቡ ሁራሪያ እንደዘገበው፡ የአላህ ሐዋርያ እንዲህ ብሏል፡፡ነፍሴበእርሱ እጅ በተያዘችው እምላለሁ በእርግጥም (ኢየሱስ) የማርያም ልጅ በመካከላችሁ ይወርዳል፡፡ ለሰው ልጆችም በፍትህ ይፈርዳል፡፡ ይሄንን የሚያደርገው ደግሞ እንደ ገዢ ሆኖ ነው፡፡ መስቀልን ይሰብራል፡፡ አሳማንም ይገድላል፡፡ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችም ቀረጥ እንዳይከፍሉ ያደርጋል፡፡ (ሳኢህ አልቡኻሪ የነቢያቶች ታሪክ ያለበት መጽሐፍ 460 3448)

በሌላ መልኩ ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜሦስተኛው ምርጫይጠፋል፡፡ ስለሆነም ክርስቲያኖች የግድ ወደ እስልምና ይቀየራሉ፡፡ ይሄንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ይገደላሉ፡፡

አሁን አሁን መሐመድ ለመስቀል ያለውን ጥላቻ የሚጋሩ እጅግ ብዙ ሙስሊሞችን ማግኘት ይቻላል፡፡

§  እንደ ጎርጎርጎርዮሳውያን አቆጣጠር 1998 . የገና በአል ከመከበሩ ከሁለት ቀን በፊት በፓኪስታን ፌይሳላባድ በምትገኝ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተንጠለጠለ መስቀል በሙስሊሞች መሪ እንዲወርድ ተደርጓል[2]፡፡

§  እንደ ጎርጎርጎርዮሳውያን አቆጣጠር በወርሀ የካቲት 18/ 2004 . በአልባንያ በምትገኝ የቅዱስ አንድሪው ቤተክርስቲያን በፎቶግራፍ የተደራጀን ማስረጃ አቅርበዋል፡፡ እንደ የፎቶግራፍ ማስረጃው ከሆነ በጣራው ላይ የተንጠለጠለን መስቀል አውርደው ሰባብረዋል[3]፡፡ በኮሶቮ አቅራብያ በሚገኝ የክርስቲያኖች የመቀበርያ ስፍራዎች በመሄድ መስቀሎችን በመነቃቀል አመጽ እንዲነሳ አድርገዋል[4]፡፡

§  እንደ ጎርጎርጎርዮሳውያን አቆጣጠር በሚያዝያ 2007 .  በባግዳድ ማለትም ክርስቲያኖች  በሰፈሩበት አል- ዳዎራ  በሚባል ስፍራ የሙስሊም አማጽያኖች ክርስቲያኖችን በቤተክርስቲያናቸው ሕንጻ ላይ የተንጠለጠሉትን በእይታ ውስጥ ያሉ መስቀሎችን እንዲያስወግዱ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን የቻለው የሙስሊሞች ህግ (ፈትዋ) የክርስቲያኖችን የመስቀል ምልክት መጠቀም  በጥብቅ ስለሚከለክል ነው[5]፡፡

§  2007 . ሀማስ ጋዛን በተቆጣጠረ ጊዜ መስቀልን የማጥፋት አመጽ አድርጓል፡፡ ጋዛ በሚገኝ የካቶሊኮች የሴቶች ገዳምና ትምህርት ቤት ጭንብል የለበሱ ወንዶች በመገኘት አካባቢውን በማመሰቃቀል፣ ዘረፋ ያካሄዱ ሲሆን ትኩረት ያደረጉትም መስቀልን ማጥፋት ላይ ነበር፡፡ በጋዛ የሚኖር የአይን እማኝ የሆነ ክርስቲያን እንደዘገበው ከሆነ በጋዛ ውስጥ ተሰሚነት ካላቸው ሰዎች አንደኛው የስቅለት ስእል ያለበትን መስቀል ከአንገቱ ጀምሮ በመቆራረጥይሄ አልተፈቀደምሲል እኩይ የሆነውን ድርጊት ፈጽሟል[6]፡፡ 

§  በጥቅምት 29/ 2007 . በዕለተ ሰኞ በማሌዥያውያን ፓርላማ ውስጥ የፓርላማ አባል የሆነ ጡሀን ሰይድ ሁድ ኢድሮስ የተባለ የፓርላማ አባል ኃይማኖታዊ የሆኑ በቤትክርስቲያኖች ትምህርት ቤቶች ፊትለፊት የሚሰቀሉ ምልክቶችን በተመለከተለኃይማኖቴ፣ ለብሔሬ፣ እንደዚሁም ለሀገሬ ሀላፊነት እንደሚሰማው ሰው ...እነዚህ መስቀሎች ድምጥማጣቸው መጥፋት አለበት ብዬ አምናለሁሲል ቁጭቱን በአደባባይ ተናግሯል[7]፡፡

§  በህዳር 2004 . እንግሊዝ አገር የሚገኝ ቤልማርሽ የተሰኘ እስር ቤት 1.6 ሚሊዮን ፓውንድ መስጊድ የማሰራት እቅድ እንዳለው ሪፖርት አድርጓል፡፡ ተቋሙ የተለያዩ ቤተ እምነቶች ለሆኑት ክርስቲያኖች ጸሎት ቤት አስገንብቶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን  ከሙስሊሞቹ ጋር በእስር ቤት የሚገኝ አንዱ የዚህን መስጊድ መሰራት ተቃውሟል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አንዳንዶቹ በሽብር ፈጣሪነት ተፈርጀው የታሰሩ ስላሉበት ነው፡፡ እነዚህ አክራሪዎች ሙስሊሞች በሚጸልዩበት ጊዜ እነዚህ የጸሎት ቤቶች መስቀላቸውን እንዳይታይ በጨርቅ መሸፈን አለባቸው ሲሉ በብርቱ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል[8]፡፡

§  በእንግሊዝ ሌላ መስቀልን የሚያጥላላ አንድ ድርጊት ተከስቶ ነበር፡፡ የለንደን ባቡር ተቆጣጣሪ የሆነው መሐመድ  አዛዊ የእንግሊዝን ዘውድ በደንብ ልብሱ ላይ ማድረጉ በፍጹም እንዳልተስማማው በብሶትና በንዴት ተናግሯል፡፡ እንደ ምክንያት አድርጎ ያቀረበው ደግሞ አነስ ያለና አምስት ሚሊ ሜትር የምትሆን መስቀል ስላለበት ነው፡፡ የሰራተኞችን ጉዳይ ወደ ሚከታተለው የከተማው ልዩ ፍርድ ቤት በመቅረብ  በከተማው የፖሊስ ተቋም ላይ ያለውን ተቃውሞ አሰምቷል፡፡ እንደ አገላለጹ ከሆነይሄ የዘር መድልዎ ነውሲል ተደምጧል፡፡ ክሱ ተቀባይነት ባያገኝም ከኃይማኖት አንፃር ዘውዱን ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆኑ  ሰዎች  ያለማድረግ ፈቃድ እንዲሰጣቸው የፖሊስ ባለስልጣኑ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡

የቀድሞው የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ጆርጅ ኬሪ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 1995 . ሳውዲ አረቢያ ደረታቸው ላይ ያንጠለጠሉትን መስቀል እንዲያስወግዱ በኃይል ተጠይቀዋል፡፡ ዴቪድ ስኪድሞር ኤጲስቆጶስ በተሰኘ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከሆነ፡

ኬሪ ከግብጽ ተነስተው ወደ ሱዳን እየበረሩ ሳለ ሳውዲ አረቢያ እንዲያርፉ አስገዳጅ ሁኔታ አጋጥሟቸው ነበር፡፡ የቀይባህር ጠረፋማ ከተማ በሆነችው ጅዳ ሲቃረቡ ኬሪ ማንኛውንም ኃይማኖታዊ ምልክቶች ማለትም አንገታቸው ላይ ያጠለቁትን ቄስ መሆናቸውን የሚያሳየውን ዘለበትና በደረታቸው ላይ ያንጠለጠሉትን መስቀል እንዲያስወግዱ ተነግሯቸዋል[9]፡፡

የቱንም ያህል መስቀል በሙስሊሞች ዘንድ የተወገዘም ቢሆን  በክርስቲያኖች ዘንድ ግን ነፃ የመውጣታችን ምልክት ሆኖ ይታያል፡፡

 

መስቀል፣ ተቀባይነትን ማጣትና እርቅ

በክርስቲያኖች መረዳት መሰረት የሰው ልጆች ትልቁ ችግር ኃጢኣት ነው፡፡ ኃጢኣት ደግሞ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያጡና  እርስበርሳቸው እንዳይቀባበሉ አድርጓል፡፡  ይሄ ባይተዋርነት ውጤቱ ደግሞ መገለልን አስከትሏል፡፡ አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመተላለፋቸው ከኤደን ገነት ተባረዋል፡፡ ስለሆነም ከእግዚአብሔር መገኘት የተገለሉ እንዲሆኑ ሆኗል፡፡ በመውደቃቸው የተነሳ ደግሞ የተረገሙ ሆነዋል፡፡

የእስራኤልን ታሪክ በምንመለከትበት ጊዜ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ከእርሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዲኖራቸው  ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ የእስራኤል ህዝብ ግን ይሄንን ሐሳብ አልተቀበሉም፡፡ ይልቁንም በራሳቸው መንገድ ተጉዘው ፍርድን በራሳቸው ላይ አምጥተዋል፡፡

በሰው ላይ የመጣውን ፍርድና   ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማጣትን ሊያሸንፍ የቻለው  ቁልፍ  ነገር መስቀል ነው፡፡  ኢየሱስ ተቀባይነትን እስከማጣት ደርሶ ራሱን ዝቅ ቢያደርግም የመስቀሉ ኃይል  ግን በሰውና በእግዚአብሔር  መካከል የነበረውን ግድግዳም ጭምር ማሸነፍ ችሏል፡፡ ኢየሱስ  ለዓለም ኃጢኣት ሲል ሰዎች የጎዱትን ጉዳት ከምንም ሳይቆጥር ነፍሱን አሳልፎ በመስጠት ለሁላችንም መስዋእት ሆኗል፡፡ በዚህ ምክንያት የሰው ልጆችን የተጣሉ እንዲሆኑ ያደረገው ኃይል መስዋእት በተከፈለበት ፍቅር ተሸናፊ ሆኗል፡፡ይሄኛው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያሳየው ፍቅር ማንው የሌለውና እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ የሰጠው ስጦታ ነው፡፡

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዷልና፡፡(ዮሐ 316)

የሰው ልጆች እግዚአብሔርን በመበደላቸው ምክንያት ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት ሊቀበሉት  የተገባቸውን ቅጣት እርሱ እንዲቀበለው ሆኗል፡፡ ይሄ የሰው ልጆች ሁሉ የተገባቸው ቅጣት ደግሞ ሞት ነው፡፡ ስለሆነም በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የኃጢአትን ይቅርታ ያገኛሉ፡፡ እንደዚሁም የዘላለም ህይወት ወራሽ ይሆናል፡፡ በዚህም መንገድ ኢየሱስ ተቀባይነት ማጣትን በተቀጣው ቅጣት እግዚእብሔርን በማስደሰት ማሸነፍ ችሏል፡፡

በሙሴ መጻሕፍት የመስዋእት ማቅረብን ምሳሌ በምንመለከትበት ጊዜ የሚፈሰው ደም ኀጢአትን ያስተሰርይ ነበር፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ይሄንን ሀሳብ የሚተረግሙት የኢየሱስ ክርስቶስን በመስቀል ላይ መሞት አስፈላጊነት ነው፡፡  በነብዩ ኢሳይያስ የባርያውን ሥቃይን አስመልክቶ የተነገረው ሐሳቡን ግልጽ ያደርገዋል፡፡

እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ እንደ ተቀሰፈ፣ እንደ ተሰቃየም ቆጠርነው፡፡ ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡ መድቀቁና መሰቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መስዋእት ቢያደርገውም እንኳ፣ ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእርሱ ይከናወናል፡፡ ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆቹ ጋር እሰጠዋለሁ፤ ምርኮውን ከኀያላን ጋር ይካፈላል፤ እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣ (ኢሳ 5351012)

ሐዋርያው ጳውሎስ ጠንካራ በሆነው የሮሜ መልዕክቱ የኢየሱስ ክርስቶስ መስዋእትነት በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረውን ተቀባይነት ማጣትን በእርቅ ፍጻሜ እንዲኖረው አድርጓል፡፡

ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኀጢአተኞች ሞቶአልና፡፡ ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል፡፡ ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቁጣው እንድናለን፤ ይህም ብቻ አይደለም ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን፡፡ (ሮሜ 56-11)

ይሄኛው የማስታረቅ ስራ በሦስተኛ አካል ማለትም የሰው ልጆችን ጨምሮ፣ በመላእክት ወይንም በአጋንንቶች የሚነሳ ማንኛውንም ኩነኔ ያሸነፈ ነው፡፡ (ሮሜ 838)

እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን  ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው? ከፍታም ቢሆን ዝቅታም ቢሆን ልዩ ፍጥረትም ቢሆንም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ፡፡ (ሮሜ 831-33 39)

ይሄ ብቻም አይደለም ክርስቲያኖች የማስታረቅን አገልግሎት እንዲያገለግሉ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡ ማለትም ለሌሎች የሚደረግ የማስታረቅ ስራ እንደዚሁም በመስቀሉ የተሰራውን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የማግኘትን መልእክት ማወጅን ያጠቃልላል፡፡

ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር   ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ ፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን (ሮሜ 2ቆሮ 518-20)

ትንሳኤና አርነት

ትንሳኤ

የመሐመድ መገለጥ ምንም ዓይነት የአቋም ለውጥ ሊታይበት ያልቻለው አርነትን አስመልክቶ የሚያንጸባርቀው መሻት ነው፡፡ ይሄንንም ለማሳካት ሲል የእርሱን ጠላቶች ለህጉ እንዲገዙ ያስገድዳቸው ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ ራሳቸውን በእርሱ መመርያና ስልጣን ሥር ያስገዙ ነበር፡፡ ይሄንን ማድረግ ባይችሉ ግን የዲህሚ ህግ ተገዢዎች እንዲሆኑ በኃይል ይገደዳሉ፡፡ ሦስተኛው ምርጫቸው ግን ሞት ነበር፡፡

የክርስቶስን አገልግሎት በተመለከተ የክርስቲያኖችን መረዳት በምንመለከትበት ጊዜ አርነት አለ ይሄ አርነት ደግሞ የተገኘው በክርስቶስ የማዳን ሥራ ነው፡፡  የተሰቃየው አገልጋይ ዓላማ ራሱን ማዋረድና  በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረውን ተቀባይነት ማጣትን ማስቀረት ነው፡፡

አርነት የመጣው በክርስቶስ ትንሳኤና እርገት ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሞትና ማንኛውም ኃይል የተሸነፈበት ስለሆነ ነው፡፡

ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ ይሄን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሳው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን ፤ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎአልና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው፡፡እንግዲህ ይህን እናንተን የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ ፡፡ (ሐዋ 231-36)

ሐዋርያው ጳውሎስ በፊሊጲስዩስ መልዕክቱ ታዋቂ በሆነው ምንባብ ላይ ኢየሱስ የቱን ያህል ራሱን እንዳዋረደ፣ በፈቃዱ የባርያን መልክ የራሱ እንዳደረገ እንረዳለን፡፡ የታዘዘውም ደግሞ እስከ መስቀል ሞት ድረስ ነው፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፡፡ በመንፈሳዊ  ስልጣናት ሁሉ ላይ የበላይ አደረገው፡፡

ይሄ በክርስቶስ የተገኘው ነፃ የማውጣት ድል በእግዚአብሔር ሉአላዊ ፈቃድ ውስጥ አስቀድሞ የነበረና በመስቀሉ የተከናወነ  ነው፡፡

እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ  ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ  ነገር አልቆጠረውም  ነገር ግን የባርያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ በምስሉም  እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳን የታዘዘ ሆነ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለልክ ከፍ ከፍ አደረገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይኽም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ …(ፊሊ 24-10)

የመስቀሉ ደቀመዝሙር

ለክርስቲያን ክርስቶስን መከተል ማለት ሞትና ትንሳኤውን ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስና ተከታዮቹ በተደጋጋሚ  ከክርስቶስ ጋር የመሞትን አስፈላጊነት አመላክተዋል፡፡ ማለት ደግሞ ወደ ሞት የሚመራውን አሮጌውን መንገድ መተውና ዳግም በመወለድ በክርስቶስ የፍቅርና የእርቅ አዲስ መንገድ በመነሳት ለራሳችን ሳይሆን ለእግዚአብሔር መኖር ነው፡፡ 

የክርስቶስን መከራ የተካፈሉ ሰዎች ልምዳቸውን ሲናገሩ በኑሯቸው ያለፈው ፈተና ድልን በሕይወታቸው እንደተቀዳጁ የታየበት፣ ተሸናፊ አለመሆናቸውም የተረጋገጠበት ነው፡፡ በዚህም ታማኝ የሆኑ አማኞችን የጭካኔ ኃይል ካለበት ከዚህ ዓለም እግዚአብሔር ነፃ እንዳወጣ ያሳየ ነው፡፡ 

በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ፡፡ ነፍሱን ሊያደን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል፡፡ (ማር 834-35 እንደዚሁም (1 ዮሐ 3 14 16 2ቆሮ 514-15 ዕብ 121-2)

ተቀባይነትን የማጣት ሁለት ወጎች

መሐመድና ኢየሱስ  በዓለም ላይ ያሉት የሁለት ታላላቅ ኃይማኖቶች መስራቾች መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ ሁለቱም ጠንካራና ቀጣይነት የነበረው ተቀባይነትን የማጣት ሁኔታ አጋጥሟቸዋል፡፡ ይሄ ተቀባይነትን  ማጣት በሁለቱም ላይ የታየው ከልጅነታቸው ጀምሮ ነው፡፡ ተቃውሞ ደግሞ የተነሳባቸው ከቤተሰብ አባላት ጀምሮ እስከ የኃይማኖት መሪዎች ጭምር ነው፡፡ ሁለቱም እርኩሳን መናፍስቶች ተቆጣጥሯቸዋል ተብለው ተከሰዋል፡፡ ሁለቱም ተፊዞባቸዋል፣ በጥብቅ ተነቅፈዋል፡፡ ሁለቱም በስቃይ ውስጥ አልፈዋል ክህደትም ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ሁለቱም በሕይወታቸው ዛቻ ነበረባቸው፡፡

እንደዛም ሆኖ እነዚህ ማንም ሊያውቃቸው የሚችሉ መመሳሰሎች እያሉ እነዚህን ሁለት ትላልቅ ኃይማኖቶች ሊለዩ የሚችሉ ልዩነቶችም አሉ፡፡ የመሐመድን የሕይወት ታሪክ በምንመለከትበት ጊዜ በአብዛኛው ለሰው ልጆች የነበረው ምላሽ አሉታዊ ነበር፡፡  ራስን አለመቀበልና ጸብ አጫሪነት ባህሪያቶቹ ነበሩ ወደ ኢየሱስ በምንመጣበት ጊዜ ግን አቅጣጫው ሙሉ በሙሉ የተለየ ነበር፡፡ አለመቀበልን ያሸነፈው በሌሎች ላይ ጫና በማሳደር አልነበረም፡፡  ይልቁንም ማፈሪያ በሚመስል ሕይወት ውስጥ በማለፍም ጭምር እንጂ፤ እንደ ክርስቲያኖች እምነት ከሆነ ተቀባይነት የማጣትን ኃይል አሸንፏል፡፡ ህመሙንም ፈውሷል፡፡ የመሐመድ ሕይወት በዲህማ ህግ መሠረት  ምን ያህል መንፈሳዊ እስራት እንዳለ ወሳኝ ነገሮችን ይዟል፡፡

የክርስቶስን ሕይወት በምንመለከትበት ጊዜ በዲህማ ህግ የሚሰቃዩትን ክርስቲያኞች ሁለንተና ነፃ የሚያወጣ ነው፡፡

 

 

 

መንፈሳዊ ንጽረተ ዓለም

እዚህ ጋር ልንጠቅሰው የተገባው ንጽረተ ዓለም የተቃኘው በአዲስ ኪዳን ነው፡፡  ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆላስይስ አማኞች በጻፈው መልዕክቱ በጸሎቱ እንደሚያስባቸው ይነግራቸዋል፡፡

እያደጋችሁ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገስ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን፡፡ እርሱ ከጨላማ ሥልጣን አዳነን ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት አፈለሰን፡፡ (ቆላ 112-14)

እንደ ጳውሎስ አመለካከት ከሆነ ሰዎች በባህሪያቸው በሰይጣንና በአጋንንቶች ኃይል ስር ናቸው፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ ባላቸው እምነት ምክንያት ከእርኩሳን መናፍስት ተፅዕኖ ነፃ ወጥተዋል፡፡ .ኤች ሀውልደን የተባሉ በኦክስፎርድ የትሪኒቲ ኮሌጅ የነገረ መለኮት  ምሑር የጳውሎስን የስነ መለኮት ንጽረተ ዓለምን አስመልክቶ ያላቸውን አመለካከት እንደዚህ ጽፈዋል፡

ስለ ሰው ማንነት የውስጥ መረዳት አለው፡፡ ሰው በአቋሙ በመጽናትና ኃጢአት በማድረግ ብቻ ከእግዚአብሔር ሐሳብ የወጣ አልነበረም፡፡ ይሄ አጽናፈ ዓለም በዲያቢሎስ ኃይላት ተፅዕኖ ስር ከመሆኑ የተነሳ እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ይልቅ ለዲያቢሎስ አምባገነናዊ አስተዳደር መገዛት ችሏል፡፡ የሰው ከእግዚአብሔር ሐሳብ ማፈንገጥ በሰው ልጆች ሁሉ ፊት የሚስተዋል የጋራ ባህሪ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ለአይሁዳውያንም ሆነ ለአሕዛብ የሚሰራ እውነት ነው፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጆች ሁሉ የአዳም ልጆች ናቸውና፡፡ (Paul’s Letters from Prison, P 18)

ሀውልደን ሐሳባቸውን ለማብራራት እንደሞከሩት የጳውሎስ ንጽረተ ዓለም የሚያሳየው የሰው ልጆች ከሰይጣን እስራት ነፃ መሆን እንዳለባቸው ነው፡፡ “(አጋንንታዊ ኃይላትን በተመለከተ የሰው ልጆች ከነሱ ተፅዕኖ ነፃ መውጣት አለባቸውገጽ 18)፡፡  ይሄንን ቁልፍ ሚና ኢየሱስ የወሰደው ደግሞ በሞትና በትንሳኤው ነው፡፡ ይሄ እውነት ደግሞ በኃጢአት ላይና የሰው ልጆችን በባርነት ተፅዕኖ ስር እንዲሆኑ ባደረጉት የዲያቢሎስ ኃይላት ላይ ድልን እንድንቀዳጅ አድርጓል፡፡

ሐዋርያው ዮሐንስ በመጀመርያው መልዕክቱ እንደጻፈው

ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን፡፡ (1 ዮሐ 519)

ጳውሎስ እንዳለው ዓለም ሁሉ በጨለማው ስልጣን (ሰይጣን) ቁጥጥር ውስጥ ከሆነ (ቆላ 113) እንደ ምሳሌ አድርገን ብንወስድ ሙስሊሞች ለክፍለ ዘመናት ተነግሮ የማያልቅን መከራ በማኅበረሰብ ላይ አድርገዋል፡፡ ይሄ ደግሞ መታየት ያለበት ከፖለቲካና ከማኅበራዊ አንፃር ብቻ አይደለም በመንፈሳዊም ጎኑም ጭምር ሊታይ ይገባል፡፡ በመንፈሳዊው ዓለም ያለው አምባገነናዊ የክፉ አሰራር በሰዎች ክልልም እንደሚሰራ የሚያመለክት ነው፡፡

ማንኛውም ሰው ሊገነዘበው የሚገባው ነገር ቢኖር  የተቋም መልክ ያላት ቤተክርስቲያን (በክርስቶስ ትምህርት የማትኖረዋ ቤተ ክርስቲያን) ከክፉ ኃይላት ተፅዕኖ ራሷን የመከላከል ብቃት ያላት አለመሆኗን ነው፡፡ ፀረ-ሴማዊነት፣ ዘረኝነት እና ሴቶችን ማግለል በውስጧ ከታዩ የማግለል ምልክቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

የክፋትን ኃይል ማሸነፍ

ለክርስቲያኖች ጎጂ ውጤት ካለው፣ መንፈሳዊ ተፅዕኖ ከሚያመጣው  የዲህሚ ሕግ ነፃ መውጣት፣ የሰይጣንን ኃይል መቋቋም እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በዚህ ዓለም ላይ ያለውን ተቀባይነት ማጣትን በመንፈሳዊ ኃይል በዋናነት የሚያቀነባብረው ሰይጣን ነው፡፡

እንደ ወንጌልና የአዲስ ኪዳን መልዕክቶች ከሆነ ሰይጣን ዓለምን የሚገዛበት ኃይል አለው፡፡ እርሱየዚህ ዓለም ንጉስነው (ዮሐ 1231)፡፡የዚህ ዓለም አምላክ” (2ቆሮ 44) እንደዚሁምየአየር አለቃ መንፈስ” (ኤፌ 22) መንግስቱ ደግሞየጨለማ ሥልጣን”  ይሄ ደግሞበማይታዘዙት ላይ የሚሰራ መንፈስነው፡፡

ኢየሱስ ለጳውሎስ በራዕይ በተገለጠለት ጊዜና ወደ አሕዛብ እንዲሄድ በጠራው ጊዜ ሐዋርያው የተነገረው ነገር ቢኖር ሰዎችንከጨለማ ወደ ብርሀን ሰይጣን ኃይል ወደ እግዚአብሔርይመልሳል ተብሎ ነው፡፡ (ሐዋ 26 18) ይሄ ሐሳብ የሚያመለክተው ሰዎች በክርስቶስ አምነው ከመዳነቸው በፊት በሰይጣን ቁጥጥር ውስጥ ነበሩ፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ በኩል በመዋጀት ከጨላማ ኃይል ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተሻግረዋል፡፡

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ከሆነ  መንፈሳዊ ጦርነት በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል ይቀጥላል፡፡ ሰይጣን ደግሞ ዓለምን ለአመጽ  የዳረገ ነው፡፡ (ማር 115 ሉቃ 1018 ኤፌ 612)  ይሄ በሁለት መንግስታት መካከል ያለ ግጭት ነው፡፡ ውግያው ደግሞ የተገለጸና ሊሰወር የማይችል ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ወደየትኛው ካምፕ መቀላቀል እንዳለባቸው መወሰን አለባቸው፡፡ ጦርነቱ ደግሞ አንድ ጊዜ በመስቀል አማካይነት አሸናፊውን ጎራ ለይቷል፡፡ ስለሆነም የፍጻሜው አሸናፊ ያለምንም ጥርጥር ክርስቶስ ሆኗል፡፡

ክርስቲያኖች እንደ ክርስቶስ ወኪል፣ እንደ ክርስቶስ ተወካዮች በየእለቱ ከጨለማ ኃይላት ጋር ሁልጊዜ ጦርነት ይገጥማሉ፡፡  የክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ የነፍሳችን ባለስልጣን በጨላማ ኃይላት ላይ ኃይለኞች ሆነን እንድንገለጥ መሠረት ሆኖናል፡፡ የዚህ መንፈሳዊ ውግያ ግዛት ደግሞ የሚያጠቃልለው ሕዝብን፣ ኅብረተሰብን፣ ማኅበረሰብናና ብሔርን ነው፡፡

የተቋም መልክ ያላት ቤተክርስቲያን በጦር ሜዳ ትመሰላለች፤ ያላት ኃይሏ ደግሞ መፈንዳት የሚጀምረው በክፉ ዓላማ ላይ ነው፡፡

ለማንኛውም እዚህ ጋር ትኩረት መስጠት የምንፈልገው ለእስልምና ነው፡፡ ቁልፉ ነገር ደግሞ መገዳደርን የሚጠይቀው መንፈሳዊና ግዛታዊ አካሄድ የሆነውን የዲህሚ ሕግና የሸሀዳ ትንታኔ ነው፡፡ በሌላው መልኩ ሙስሊሞችን የበላይና የተማሩ አድርጎ በማቅረብ ሌሎቹን ባርያ በማድረግ መጨቆን፣ በሌላ መልኩ ክርስቲያኖችንም ባርያ ማድረግና ሌሎች ሙስሊሞች ያልሆኑት ሕዝቦች ዝቅ ብለው እንዲገዙ ማድረግ፤ የሀሰት ምስጋና በመስጠት ዝም ብለው እንዲገዙ በማድረግ በሞት እርግማን ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋሉ፡፡ (ኤፌ 611-17)

ሐዋርያው ጳውሎስ ስላገኘነው ድል አስረግጦ ሲናገር የዚህ ዓለም ገዢ የሆኑት የጨለማ ኃይላት ትጥቃቸው ተፈትቷል፣ አቅማቸው ተወስዷል፡፡ ተሸናፊዎችም ሆነዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ሊሆን የቻለው በመስቀሉ በተሰራው የኃጢአት ይቅርታ ነው፡፡

እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለ መገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ፡፡ በደላችሁንም ሁሉ ይቅር አላችሁ፡፡ በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽህፈት ደመሰሰው፡፡ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፡፡ አለቅነትና ሥልጣናትን ገፎ ድል በመንሳት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው፡፡ (ቆላ 213-15)

ዲህማና ሸሀዳ  የተጻፉ መለያዎች ሆነው የሰው ልጆችን ስብእናን በመቃወምም ጭምር ያገለግላሉ፡፡ የመንፈሳዊው ኃይል መለያዎች የሆኑት ሰዎችን የሚቀወሙትና የሚጨቁኑት ዲህማና ሸሀዳ በመስቀሉ ኃይል በሚስማር ሊጠረቅባቸው ችሏል፡፡  ይሄ ደግሞ በአደባባይ የሚያሳዩትና እን ሦስተኛው ምርጫ  ብዬ ያልኩትንም ጭምር  የሚያጠቃልል ነው፡፡

የዲህማ ሕግ ቁልፍ የሆነው አካሄዱ ኢስላም ያልሆኑትን በዝምታ ማስጨነቅ ላይ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ነገር ግን በመስቀሉ በመጠረቁ ትጥቁ ተገፎ ጥርስ እንደሌለው አንበሳ ሆኗል፡፡ ከዚህም የተነሳ ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ ኃይላትና ሥልጣናት ላይ ድልን እንደተቀዳጁ ሁሉ በዲህሚ ህግ ላይም አሸናፊዎች ናቸው፡፡

ሕጋዊ መብቶች

መንፈሳዊ ነፃነትን የምንቀዳጅበት አንደኛው ደረጃ ሰይጣን በኛ ላይ ያወጀብንን አዋጅ በመንፈሳዊ ሥልጣን በመቃወም ነው፡፡ መንፈሳዊ መሰጠት በቀደመው ትውልድ ሲኖር፣ ደግሞም በክርስቶስ የተሰራውን ሥራ በእምነት መቀበል ሲቻል ቀጣዩ ተውልድ በነፃነት እንዲመላለስ ሁኔታዎች ይመቻቹለታል፡፡ እውነቱን በምንመለከትበት ጊዜ ሰይጣን በክርስቲያኖች ላይ ቀጣይነት ያለው መንፈሳዊ ውግያ ለመክፈት ኪዳን እንደገባ ከስራው መረዳት እንችላለን ፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚያስተምረው ከሆነ ቁጣን ደብቆ በመያዝና በማሰላሰል ለዲያቢሎስ ዕድል ፈንታን መስጠት ይቻላል፡፡

ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ ለዲያቢሎስም ፈንታ አትስጡት (ኤፌ 4 26)

እዚህ ላይ  “ፈንታየሚለው ቃል የተተረጎመው ቶፖስ ከሚለው የግሪክ ቃል ነው፡፡ ትርጓሜው ደግሞ በአንድ አካባቢ መሆን ወይንም የተያዘ ቦታ ማለት ነው፡፡ቦታ መስጠትየሚለው ሐሳብ ደግሞእድል ፈንታንአሳልፎ መስጠት እንደ ማለት ነው፡፡  ስለዚህ ጳውሎስ እያለ ያለው አንድ ሰው ለኃጢአቱ ይቅርታን ከመጠየቅ ይልቅ በመቆጣት ሸምቀቆ ውስጥ ራሱን ቢያስገባ ለክፉ ሐሳብ ዓላማ መጠቀምያ ለመሆን መሠረትን ያመቻቻል ማለት ነው፡፡

በዮሐ 14 30 ኢየሱስ ክፉው በእርሱ ላይ እድል ፈንታ እንደሌለው መናገሩ ትክክለኛ መሠረት ነበረው፡፡

 ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ ነገር ግን አብን እንድወድ ዓለም ሊያውቅ አብም እንዳዘዘኝ እንዲሁ አደርጋለሁ፡፡ ተነሡ፤ ከዚህ እንሂድ፡፡ (ዮሐ 14 30-31)

ሊቀ ጳጳስ . ኤች በማብራርያ መጽሐፋቸው እንዳስቀመጡት ኢየሱስ እየተናገረ ያለውብታሰር እንኳን ሰይጣን በማንነቴ ላይ ምንም ማድረግ አይችልምየሚል ነው፡፡ (A critical and Exegetical Commentary on the Gospel According to John, Vol 2, P. 256). ይሄኛው ፈሊጣዊ አነጋገር በእርግጥ ተገቢ መሆኑ በካርሰንም ማብራርያ ተሰጥቶበታል፡

በእኔ ላይ አንዳች የለውም የሚለው አባባልበእኔ ላይ ምንም ማድረግ አይችልም”    የእብራውያንን አነጋገር በምንመለከትበት ጊዜበእኔ ላይ ምንም መናገር አይችልም”   ‘ሊነቅፍብኝ የሚችለው ምንም ነገር የለውምየሚል ነው፡፡ ዲያቢሎስ በኢየሱስ ላይ አንዳች ነገር ሊያደርግ የሚችለው እሱን ሊከስበት የሚችል ነገር ማግኘት ሲችል ብቻ ነው፡፡(The Gospel According to John PP.508-9)

ምንም ዓይነት ኃጢአት ያልተገኘበት ኢየሱስ አባቴ ያዘዘኝን አደርጋለሁ ብሏል፡፡ ለዚህም ነው ሰይጣን በሱ ላይ   አንዳች ለማድረግ ምንም ሕጋዊ መሠረት ሊያገኝ ያልቻለው፡፡ ይሄ ደግሞ የመስቀሉን ሚስጥር እንድንረዳ ትልቅ አቅም ይሆነናል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢየሱስ ሞት ሰይጣን ሕጋዊ ቀጪ እንዳይሆን መሠረቱ ሁሉ እንዲፈራርስበት አድርጓልና፡፡

ጌታ የሆነው መሲህ መሞቱ በሌሎች ምትክ የተደረገ ንጹህ መስዋእት ነው፡፡ ሰይጣን በኢየሱስ ላይ ያደረገው ቅጣት ተደርጎም መቆጠር የለበትም፡፡ ኢየሱስ የሚነቀፍበት ነገር ከሰይጣን ዘንድ ተገኝቶበት ቢኖር ኖሮ የተሰቀለው ስለ እርሱ ኃጢአት በሆነ ነበር ነገር ግን ንጹህ ከመሆኑ የተነሳ የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማስወገድ መስዋዕት ሆኗል፡፡

የመግቢያ ቀዳዳዎችን መድፈን

ስለ መንፈሳዊ ነፃነት በምንነጋገርበት ጊዜ አስፈላጊና ስሜትን የሚነካ ጉዳይ ስለሆነ ስልታዊ በሆነ መንገድ ሊታይ ይገባዋል፡፡ በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ ማንኛውንም ለዲያቢሎስ እድልፈንታ የሚሰጥን ነገር ማስወገድና በሮችን ሁሉ መዝጋት እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ወደ በሩ መቅረብ ማለት ደግሞ አንድ ሰው ለሰራው በደሉና ለተናገራቸው ከንቱ ንግግሮች ንስሀ በመግባት ሰይጣን በሕይወታቸው የፈቀደውን እንዲያደርግ መብት ከሰጡት ማንኛውም ነገር መላቀቅን የሚያሳይ ነው፡፡

መስቀሉ ለማንኛውም መንፈሳዊ ጥያቄ መፍትሔ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ክርስቶስን እንደ አዳኝ አድርጎ በመቀበል፤ በግሉ የእግዚአብሔርን ይቅርታ ማግኘት ይችላል፡፡ ከክርስቶስ ጋር በመቀበር ከእርሱ ጋር የታወቀ ይሆናል፡፡ ከዚህም የተነሳ የሰይጣን ሕጋዊ የሆነ ክስ ማቅረብ አይችልም፡፡ይሄ ማለት ደግሞ በክርስቶስ ከመሆኑ የተነሳ አንዳች ነቀፌታ ሊያገኝበት አይችልም፡፡ ነቀፌታው በመስቀሉ ተወስዷልና፡፡

አንድ ሰው የማያቋርጥ የመዋሸት ሕይወት በሚኖረው ጊዜ ሰውየው መዋሸቱ በእግዚእብሔር ፊት ስህተት እንደ ሆነ ያውቃል፡፡ ስለዚህም ይሄንን በመናዘዝ፣ ንስሃ በመግባት በክርስቶስ በኩል የኃጢአትን ይቅርታ ያገኛል፡፡

ትውልድ ተሻጋሪ መንገድ

በአንዳንድ ቤተሰቦች ከሚያነሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ አንድ ስህተት ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ ጉዳት  ሊያስከትል ይችላል የሚል እምነት ነው፡፡ አብዛኞቹ የሚስማሙበት ነገር ቢኖር ከዘር የሚወረስ ወይንም ከማኅበረሰቡ የሚወረስ ነገር በመልካምም ሆነ በመጥፎ ሁኔታ በቤተሰብ ላይ ተፅዕኖ ሊያመጣ ይችላል የሚል ነው፡፡  መጠየቅ የሚገባው ጥያቄ ግን በእርግጥም ቤተሰብ መንፈሳዊ ነገርን ለትውልዱ ማስተላለፍ ይችላልን? የሚል ነው፡፡ ማስተላለፍ የሚችሉ ይመስላል  አንዳንድ ተፅዕኖዎች ደግሞ ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገሩ ናቸው፡፡ መንፈሳዊ ተፅዕኖ እጅግ ብዙ ትውልድን የመጉዳት አቅም አለው፡፡

አንዳንድ ክርስቲያኖች ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ መንፈሳዊ ቀንበር አለ በሚለው አስተሳሰብ አይስማሙም፡፡ ሊቀበሉትም አይፈልጉም፡፡ ምክንያታዊም አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ፡፡ ምናልባት በቤተሰብ ላይ ያለ ባህሪ ወደ ልጆች ሊተላለፍ ይችላል ብለው ግን ያምናሉ፡፡ እንደ ምሳሌ አድርገን ብንወስድ ወላጆች ውሸታም ከሆኑ ልጆች ይሄንን እኩይ ባህሪ መቅዳት ይችላሉ፡፡ከዚህም የተነሳ ውሸታም መሆንን ይማራሉ፡፡ ወይንም እናት ልጇን የምትጋገም ከሆነ ልጁ ማንነቱን በተመለከተ ደካማ አመለካከት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡

አጠቃላዩን የመጽሐፍ ቅዱስ ንጽረተ ዓለም ከቃልኪዳን፣ እርግማንና በረከት አንጻር በምንመለከትበት ጊዜ በእነዚህ አመለካከቶች የተቃኘ ነው፡፡ የሙሴ መጽሐፍ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ስለገባው ኪዳን ይናገራል፡፡ በነሱና በትውልዳቸው መካከል ሊተላለፍ ስላለው በረከትና መርገም የሚናገር ነው፡፡ በረከቱም ለሺህ ትውልድ ሲሆን እርግማኑ ደግሞ ለሦስትና አራት ትውልድ ነው፡፡ (ዘጸ 205 347)  

በተጨማሪም ትውልዱ ከአባቶቻቸው በደል ነፃ ይሆን ዘንድ የእነሱንና የአባቶቻቸውን በደል የግድ መናዘዝ አለባቸው፡፡ (ዘሌ 2640) ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል፡፡ለአባቶቻቸው የገባውን ኪዳን ያስታውሳል ፡፡ ምድራቸውንም ይፈውሳል፡፡

 

ሸሀዳን ለመተው የሚደረግ ምስክርነት

እስልምናን ካደው!”

ክርስትናን ያጥላላ የነበረ የቀድሞ ሙስሊም ምስክርነት

ተወልጄ ያደግኩት በምዕራቡ ዓለም ከሚኖሩ የሙስሊም ቤተሰብ ነው፡፡ መስኪዶች በመሄድ   ኃይማኖታዊ ሥርአት ከመፈጸሜም በተጨማሪ ጸሎትን በአረብኛ እንድንጸልይ ትምህርት ይሰጠን ነበር፡፡ በእርግጥ ይሄ ነው የሚባል አክራሪ ኃይማኖተኛም አልነበርኩም፡፡  ነገር ግን ወደ ዩኒቨርሲቲ ከገባሁ በኋላ ግን ባለጠበቅኩት ሁኔታ ነገሮች መቀየር ጀመሩ፡፡ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ  ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን እንደሆነ እንደሚገባ ተረዳሁ፡፡ በእርሱም አምኜ ነፍሴን አዳናት፡፡

በትምህርት ላይም ሳለሁ በክርስቲያኖች ቡድን ውስጥ ታቅፌ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮችን መሳተፍ ጀመርኩ፡፡ በየሳምንቱ የተለያዩ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ያካፍሉናል፡፡ በክርስቶስ አምኜ ዓመት እንኳን ሳይሞላኝ መልዕክት እንዳካፍል ተጠየቅኩ፡፡ መልዕክት በማካፍልበት አንድ ምሽት ላይ ለመጸለይ በዩኒቨርሲቲው አንደኛው ቤተመጻሕፍት ለመጸለይ ሄድኩ፡፡ መልዕክቴ ደግሞኢየሱስ ለኔ ሞቷል እኔስ ለኢየሱስ እሞታለሁ?” የሚል ነው፡፡

ታድያ መጸለይ በጀመርኩ ጊዜ አንድ ያልተጠበቀ ነገር ሆነ በጉሮሮዬ አካባቢ የአየር እጥረት እንዳጋጠመው ዓይነት ስሜት ተሰማኝ ፡፡ የሆነ ለየት ያለ ነገር ሁለንተናዬን ሲቆጣጠር ይታወቀኛል ፡፡ ከዚያም አንድ ድምጽ  “እስልምናን ካድ እስልምናን ካድ”  ብሎ ሲናገረኝ ሰማሁ፡፡ ጌታ እንደሆነ አመንኩ፡፡ እኔምጌታ ሆይ እኔ እኮ በእርግጥም ኢስላም አይደለሁም በልምምዱ ውስጥም የለሁምአልኩ፡፡

ቢሆንም በአየሩ ላይ የከበደ ነገር አሁንም አለ፡፡እስልምናን ክጄአለሁይሄ ሁሉ ነገር የሆነው በዝግታ መንፈስ ውስጥ ሆኜ በቤተመጻሕፍት ውስጥ ሆኜ ነበር፡፡ ወዲያውኑ ጉሮሮዬ ውሰጥ የነበረው ነገር ለቀቀኝ፡፡  ለየት ያለ የእረፍት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ወደ ጸሎትና ዝግጅት ከሄድኩ በኋላ  ወደ ስብሰባችን ስፍራ አመራሁ፡፡ በስብሰባችን ጌታ በኃይል ተገለጠ አስታውሳለሁ ተማሪዎች በጉልበታቸው ተንበርክከው እያለቀሱ ራሳቸውን ለጌታ ይሰጡ ነበር፡፡

አዲስ አማኞችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ

በሰሜን አሜሪካ የሚገኝ አንድ አገልግሎት ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉትን ከእስልምና ወደ ክርስትና ለተለወጡ ሰዎች የማይቆም ስልጠና ይሰጣል፡፡ የስልጠናው አስተባባሪ አንድ የተረዳው ነገር ቢኖር ተሳታፊዎቹ ጽኑ የሆኑ ደቀመዛሙርት የመሆን ችግር ነበረባቸው፡፡

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው ሸሀዳን መተው አስመልክቶ ስለሚናገረው ጸሎት እውቀቱ አላቸው፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች ሁሉ በአንድ ላይ በመሰብሰብ እስልምናን ሙሉ በሙሉ ከሕይወታቸው እንዲያስወጡ ጸልየዋል፡፡ የተሳታፊዎቹ ምላሽ የሚያመለክተውም ታላቅ ዕረፊትና ደስታ እንደተሰማቸው ነው፡፡  “እልምናን ሙሉ በሙሉ ማስወጣት እንዳለብን ለምንድን ነው ማንም ግልጽ አድርጎ የማይነግረን ይሄንን ደግሞ ከረዥም ጊዜ ማድረግ ነበረብንሲሉ ይጠይቃሉ፡፡  እስልምናን በአደባባይ መካድ የስልጠናው አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡

 

 

ዲህማን በመካድ ስለመጣ ለውጥ የተሰጠ ምስክርነት   

ትውልድ ተሻጋሪ ፍርሃት

በዘመኗ ሁሉ በታላቅ ፍርሃት ውስጥ ለነበረች ሴት የመጸለይ እድል ገጥሞኝ ነበር፡፡ ዘሮቿ በደማስቆ ሶርያ ከአንድ መቶ ዓመት በፊት በዲህማ ተፅዕኖ ስር ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡ የታወቀው ክርስቲያኖችን በጅምላ እንዲጨፈጨፉ በተደረገበት 1860 . ማለት ነው፡፡ በዲህማ ተፅዕኖ ስር ላሉት አሰራሩን በመካድ በምንጸልይ ጊዜ የፍርኃት መንፈስ ተሰበረ፡፡ ከዚህም የተነሳ ለዘመናት ከእርስዋ ጋርየነበረው ፍርሃት ተነስቶ እረፍትን አገኘች፡፡

ከዘር ማጥፋት ውርስ ነፃ መውጣት

ከአርሜንያን  ቤተሰቦች የተወለደ ሰው ዘሮቹ የግሪክ ስም ስነበራቸው ብቻ በጅምላ ግድያ ውስጥ ማለፍ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ የተረፉት ቅሬታዎች በሰምሪኒያ አድርገው ወደ ግብጽ  መጥተዋል፡፡  ከአንድ ክፍለዘመን በኋላ ይሄ ልጅ በየእለቱ በእንደዚህ ዓይነቱ ፍርሃት ውስጥ ያልፍ ነበር፡፡ የቤቱን በሮችን መስኮቶች መዝጋቱን እርግጠኛ እስካልሆነ ድረስ ከጭንቀት ነፃ አይሆንም ነበር፡፡ እንደዛም ሆኖ ከትውልድ ትውልድ እተላለፈ የመጣውን የፍርሃት መንፈስ በካደና አብረን በጸለይን ጊዜ ለየት ያለ ነፃ መውጣትና መንፈሳዊ ፈውስ በሕይወቱ ተከናወነ፡፡

 

 

ከፍርሃት ወደ ድፍረት - ወንጌልን የማድረስ ሥልጠና

አረብኛ ተናጋሪ የሆኑ ክርስቲያኖች በቡድን ሆነው ይጸልዩ ነበር፡፡ የሚጸልዩትም  ወደ አውሮፓ ሀገራት ቱሪስት ሆነው ለጉብኝት ለሚመጡት ሙስሊሞች ወንጌልን ለመስበክ ነው፡፡ የቱንም ያህል የወንጌል ቡድኑ ያለው ነፃነት ባለበት ምድርም ቢሆን እምነታቸውን በድፍረት ለመናገር ፈርተው ነበር፤ ከዚህም የተነሳ ከፍርሃት ቀንበር ወጥተው ውስጣቸው እንዲፈወስ ግልጽ ውይይት ማድረግ ነበረባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በመካከላቸው የነበረ አንድ መሪ ገላጻውን እንዲህ ሲል አሰማ  “በውስጣችሁ ታላቅ ፍርሃት ሊፈጠር የቻለው በናንተ ፈንታ ተገብቶ የነበረ ኪዳን ስላለ ነው፡፡ በንግግሩ ላይ ከተወያዩ በኋላ  ከዚህ በፊት በማስገደድ ተገብቶ የነበረውን ቃል ኪዳን አስመልክቶ ብርቱ ጸሎት በማድረግና ሥራውን በመካድ ነፃ መሆን ተችሏል፡፡

ውጤቶቹ እጅግ አስገራሚ ነበሩ ፡፡ ያለምንም ልዩነት የዚህ ጸሎት ተሳታፊዎች ሐሳባቸውን በኃይል ለመግለጽ  እንደሞከሩት በስልጠና ውሥጥ እንደዚህ ዓይነቱ ርዕሰ ጉዳይ የግድ መካተት አለበት፡፡ ለጥልቅ በረከትና እውነተኛ ነፃነት በተለይም ደግሞ እያንዳንዱ ሰው በዲህማ የተገባን ቃልኪዳን በመካድ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ያገኙትን ኪዳን አውጀዋል፡፡  ከዚህ ተፅዕኖ ነፃነት ስላለ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ በደሙ ኃይል በጸሎት ነፃ  መውጣት ችለዋልና፡፡

 

 

የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ተከታይ የሆነች ሴት ሙስሊሞችን በወንጌል ለመድረስ እንዴት ኃይል እንዳገኘች የሰጠችው ምስክርነት

በሙስሊም ሀገር ለአራት ዓመት ተምሬ በሕግ የመጀመርያ ዲግሪዬን ስሰራ ሼሪያን የትምህርቱ እንደዋና ክፍል ተቆጥሮ የማጥናት እድል አግኝቼ ነበር፡፡ በሼሪያ ሕግ መሰረት ክርስቲያኖችን እንዴት ዝቅ ማድረግ እንደሚቻል በጥልቀት አጥንቻለሁ፡፡ የዲህማ ሕግንም ጭምር ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር እንደዚህ ዓይነቱ አስተምህሮ በኔ ባህሪ ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ በተመለከተ በነበረኝ መረዳት ላይ ያጋጠመኝ እንቅፋት ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን የምወድ የተሰጠሁ ክርስቲያን ነበርኩኝ፡፡ ነገር ግን ስሜቶታቸውን እንዳልጎዳ በማሰብ ጌታዬን በሙስሊም ወዳጆቼ ፊት የመመስከር አቅም አጣሁ፡፡ የዲህማ አካሄድን አስመልክቶ የተዘጋጀን ጥናት በተካፈልኩ ጊዜ ያለሁበት መንፈሳዊ ሁኔታ ወደ ብርሃን መውጣት ጀመረ፡፡ ከነፍሴ ውስጥም ትልቅ ተስፋ መቁረጥ ፈንቅሎ ወጣ፡፡ ያባቶቼን ምድር ድል ባደረጉባቸው ቦታዎች ላይ ሙስሊሞች የበላይ ሆነው መግዛታቸውን በደስተ የተቀበልኩባቸውንና እንዲያውም ስለ ትክክለኛነቱ የተሟገትኩባቸውን ጊዜያት አስታውሳለሁ፡፡ ለረዥም አመታት የዲሚን ሕግ ተቀብዬ ተረግጬ የኖርኩ መሆኔን ልክድ አልችልም፡፡ የጸሎትን ኃይል ተመልክቻለሁ፡፡ በክርስቶስ ያገኘሁትንም አርነት መለማመድ ችያለሁ፡፡

በተመሳሳይ ምሽት ተመልሼ ወደ ቤቴ ሄድኩና የቅርብ ወዳጄ የሆነችን አንዲት ሙስሊም ጠራሁ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወዳትና በመስቀል ላይ እንደሞተላት ነገርኳት፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለሙስሊሞች የምሰጠው አገልግሎት እጅግ ውጤታማ ሆነ፡፡ ብዙዎቹ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ጌታና አዳኝ ሲያውጁት ማየት ችያለሁ፡፡

የደም ቃልኪዳንና ልምምዱን በይፋ መካድ  

ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው ሌላው ቁልፍ የሆነ ፅንሰ ሐሳብ ቢኖር ዲህማ ማለትየደም ቃልኪዳንመሆኑን ነው፡፡ በእብራውያን ቅዱሳን መጻሕፍት ደረጃውን የጠበቀ ቃልኪዳን የሚገባውና አንድ ሰው በዚህ ቃልኪዳን የሚታሰረው የደም መስዋዕት በማቅረብ ነው፡፡  በዘፍ 15 ላይ እግዚአብሔር በጣም ታዋቂ የሆነውን ኪዳን ለአብርሃም ሲገባ መስዋእት በመጠየቅ ነው፡፡ አብርሃም እንስሳውን አዘጋጀ፡፡ እንስሳውን አረደና የሥጋውን ብልቶች ቆራርጦ መሬት ላይ አስቀመጠ፡፡ ከዚያም የእግዚአብሔርን መገኘትና ተሳታፊ መሆን የሚያመለክት የሚጨስ ነበልባል በሥጋው መካከል አለፈ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ልምምድ እርግማንን ይቀሰቅሳል፡፡ የዚህ ቃል ኪዳን መልዕክት በግልፅ ቢነገርም ባይነገርም ባለ ቃልኪዳኑ የሚናገረው ንግግር፡ቃል ኪዳኑን ካፈረስኩ እኔም እንደ እንስሳው ይሁንብኝማለት ነው፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ መገደልና መቆራረጥ ማለት ነው፡፡

ይህ ነገር እግዚአብሔር በነብዩ ኤርሚያስ በኩል በተናገረው ነገር ውስጥ ተንጸባርቋል፡

ቃል ኪዳኔንም የተላለፉትን ሰዎች፥ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳንን ቃል ያልፈጸሙትን፥ የይሁዳን አለቆችና የኢየሩሳሌምን አለቆች ጃንደረቦችን ካህናትንም በእንቦሳም ቍራጭ መካከል ያለፉትን የአገሩን ሕዝብ ሁሉ፥ ለጠላቶቻቸው እጅ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል። ኤር 3418-20

ጠንቋዮች የሚለማመዷቸው በባዕድ አምልኮ ውስጥ የሚገኙ ልምምዶች የደም መስዋዕትን በመጠቀም ሰዎችን በቃል ኪዳን የማሰር ተግባርን ሊያካትት ይችላል፡፡ በሌሎች የባዕድ አምልኮ ቡድኖች ውስጥ ደግሞ ሞትን በራስ ላይ መጥራት፣ ለምሳሌ ያህል ራስን በመርገም፣ የሞት ምልክት የሆውን ሸምቀቆ አንገት ላይ በማሰር፣ ሞትን የሚያመለክቱ ነገሮችን በማድረግ ለምሳሌ ያህል በሬሳ ሳጥን ውስጥ በመግባት፣ ጦርን ልብ ላይ በማድረግ ቃል ኪዳን ሊፈጸም ይችላል፡፡ ባሕላዊ በሆነው የእስልምና የጂዝያ አከፋፈል ጊዜ የሚደረገው ሙስሊም ያልሆነውን ሰው አንገት የመቅላት ምልክት የደም መስዋዕት ምልክት ነው፡፡ ይህ ስርኣት ዲህሚው በራሱና በሕብረተሰቡ ላይ የሚያመጣውን አንገት መቀላት የሚያመለክት ነው፡፡ እርሱም በመንፈሳዊው ዓለም እንዲህ እንደማለት ነው፡የዚህን ውል አንዱንም አንቀጽ ብተላለፍ አንገታችን እንዲህ ይቀላ፡፡

ግልፅ እና ስውር የሆኑ የደም ቃልኪዳን እርግማኖች አደገኛ ናቸው ምክንያቱም መንፈሳዊ ባርነትን ሊያስከትሉ ይችላሉና፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ሰውየውን በውሉ የታሰረ እንዲሆን ያደርጉታል በመቀጠልም በውሉ ላይ በሰፈረው እርግማን መሰረት ሰውየው በአዕምሮም ሆነ በመንፈስ የተጨቆነ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡

የነዚህ እስራቶች መገለጫዎች በጣም አስደናቂ ናቸው፡፡ አንዲት የዲህሚ ታሪክ የነበራት ሴት የሞቱ ዘመዶችዋ ወደ ሙታን ምድር ትመጣ ዘንድ በህልሟ ያባርሯት ነበር፡፡ ያለ ምንም ምክንያት ደግሞ ራሷን ለመግደል ትፈልግ ነበር፡፡ እየጸለይንና እያወራን በመጣን ቁጥር ቤተሰቦችዋም በተመሳሳይ ሁኔታ በቅዠት ይሰቃዩ እንደነበር ተረዳን፡፡ ዘሮችዋ ለረጅም ዘመናት በዲህማ ውስጥ ይኖሩ ስለነበር የሞት ፍርሃት እያስጨነቃት መሆኑን ተረዳሁ፡፡ ዘሮችዋ በዓመታዊ የጂዝያ ክፍያ ስርኣት ውስጥ በመሳተፋቸው ምክንያት የመጣውን የሞትን ኃይል እየገሰፅን እና እያንዳንዱን የሞት እርግማን እየሰበርን መጸለይ ጀመርን፡፡ ከዚህ ጸሎት በኋላ ያቺ ሴት ከቅዠት እና ከሞት ፍርሃት ነፃ ወጣች፡፡

በእስራት ውስጥ ያሉትን የመፍታት ስልጣን

አርነት መውጣትን የሚከለክል ተቃውሞ በሚመጣበት ጊዜ ሊወሰድ የሚገባው እርምጃ ቢኖር እግዚአብሔራዊ ያልሆነን ማንኛውንም አካሄድ ለመቃወም ፈጣን እርምጃ መውሰድ ነው፡፡ ብሉይ ኪዳንን በምንመለከትበት ጊዜ ጣዖታትና የሚመለኩባቸው ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ ወድመው ነበር፡፡ ይሄ ደግሞ የሚያሳየው ጣዖታት ምንያህል በመንፈሳዊው ስፍራ ግዛት እንደነበራቸው ነው፡፡ (ዘዳ 121-3) ከፍተኛ ቦታዎች፣ የጣዖት ልምምድ የሚደረግባቸው ስፍራዎች፣ ለጣዖት የሚሰዋባቸው እቃዎች እና መስዋእታቸው ሙሉ በሙሉ ጣዖታቱንም ጨምሮ እንዲወገዱ ተደርጓል፡፡

አንድን ስምምነት ለማድረግ በሚታሰብበት ጊዜ እያንዳንዱ ነገር በጥንቃቄ መታየት አለበት፡፡ ሊታይ የሚገባው ደግሞ ሁኔታውና ሊያስከትል የሚችለው ውጤት መሆን አለበት፡፡ ይሄ ደግሞ የሚኖረው ጠቀሜታ ምንድን ነው ካልን አንድን ኃጢኣት በደንብ አውቆ ለመናዘዝና ንስሃ ለመግባት ስለሚጠቅም ነው፡፡ መንፈሳዊ ነፃነትን ለማወጅም ይጠቅማል፡፡ ይሄ ደግሞ ማንም በየትኛውም ይቅርታ በሚያስፈልገው የሕይወቱ ክፍል የእግዚአብሔር የእውነት ብርሃን እንዲያንጸባርቅበት ያደርጋል፡፡

እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ ቃልኪዳኖች በሚደረጉ ጊዜ ተመሳሳይ የሆነ መርህ መተግበር አለበት፡፡ ለምሳሌ ያህል አንድ ሰው ዝም ለማለት የደም ቃል ኪዳን ቢገባ ይህንን የደም ቃል ኪዳን ለመስበር ንስሃ መግባት እና የዚህን ቃል ኪዳን ተሳትፎ መካድ ያስፈልገዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታእኔ ይህንንና ያንን ጉዳይ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ይቅር አልልምበማለት ከመናገራቸው የተነሳ ይቅርታ ካለማደረግ መንፈስ ጋር የሚታገሉ ሰዎች ይህንን መሃላ በመካድ እና በእግዚአብሔር ፊት ንስሃ በመግባት እርግማኑን ሊሰብሩት ይገባል፡፡ ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸው በሞት ስለተስፈራሩ የደረሰባቸውን በደል ላለመናገር ቃል የገቡ ሰዎችየደረሰብኝን ነገር ላለመናገር የገባሁትን የዝምታ ቃል ክጄ ስለመብቴ እሟገታለሁበማለት መሃላውን መስበር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከዲህማዊነት መንፈስ ነፃ ለመውጣት የመፈልግ ሰው የጂዝን ክፍያ እና አንገት ላይ የሚደረገውን የእርድ ምልክት መካድ ግድ ይለዋል፡፡

ኢየሱስም ለደቀመዛሙርቱ በሰማይና በምድር የማሰርና የመፍታት ስልጣን እንዳላቸው ነግሯቸዋል፡፡ ህም ማለት በመንፈሳዊው ዓለም እና በቁሳዊው ዓለም ማለት ነው፡፡

እውነት እላችኋለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል (ማቴ 1818 1619)፡፡

ክርስቲያኖች እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ ውሎችንና ስግደቶችን  የማፍረስ ስልጣን እንዳላቸው ማወቁ አስገራሚ መጽናኛ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ደም የተደረገው ቃል ኪዳን ማንኛውንም በክፉ ሐሳብ የተሰራን ውልና ኪዳን ስለሚያፈርስ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ መሲሁን አስመልክቶ በዘካርያስ መጽሐፍ የተጻፈው ነው፡፡   

ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጉድጓድ አውጥቻሁ (ዘካ 911)

በመስቀሉ አማካይነት በአለቆችና በጨለማ በስልጣነት ላይ ድል እንዳለ እግዚአብሔር አስቀድሞ አሳውቆናል (ቆላ 213-15)፡፡ ይሄኛው ድል የክፋት ኃይላት የሚገዙበትን ሰዎች በፈቃዳቸውም ይሁን ያለፈቃዳቸው አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በነሱ ቅጥጥር ስር እንዲሆኑ ያደረጉበትን  ኃይላቸውን ማሳጣት ችሏል፡፡

 


[1]  W.Muir, The life of Muhammad. Volume3, p.61, note 47

[2]  Annual Report on International Relegious Freedom for 1999. US State  Department <http//www.thepersecution.org/used/us99irf.html>

[3]  ERP-KLM Info Service. Newsletter 17/3/ 2005. <http:// www.Kosovo. Net/news/ archive/2005/ March_17/1. Html>

[4]  Jared Israel, “ Eradication of an ancient culture… The destruction of the Churches of Kosovo’.<http:// emperors clothes.com list.htm>.

[5]  Extrimists threaten Church in Baghdad’. Zenit News Service. 19 April 2007. <http://www.zenit.org/article/19414?I=english>

[6]  Fears in PA : Gaza May  turn into Taliban-style Emirate. MEMRI Special Dispatch Series 1633, Palestinian Authority / Jihad & Terriorism Studies Project, June 26, 2007. <http:// memri.org/ bin/articles.cgi? page= archives& Area=sd&ID= SP 163307> This is cited from  AL-Quds AL- Arabi (London), June 20, 2007.

[7]  The Hansard record of the Third Meething of the fourth Session of Eleventh Parliament (Dewan Rakyat) of Malasia, on Monday, 29 October 2007, PP. 143-44http://www.parlimen.gov.my/hidex/pdf/DR-29102007.pdf.

 

[8]  Reported by Justin Penrose,  writhing in the Sunday  Mirror  of November  7.2004. Daniel Pipes  offered  a critique  of this dission in his ‘ Londonistan  Follies’ blog http://www.danielpipes.org/blog /298.

[9]  David Skidmore . ‘Heart speaks to heart during Archbishop of Canterbury ‘s visit to Chicago.’ www.wfn. org /1996/06/ msg 00144.htm.