አጫጭር ዜናዎች
አክራሪ ሙስሊሞቹ አፍሪካ ባሉ ክርስቲያኖች ላይ ጦርነት አፋፍመዋል
International Christian Concern Washington, D.C. 07/06/2012
በጆናታን ራኮን (Jonathan Racho )
አለም አቀፍ የክርስቲያን ተቆርቆሪ ድርጅት (International Christian Concern) ጁላይ 06, 2012 ባወጣው ዜና ላይ ጆናታን ራኮ ያቀረበውንና አክራሪ የሙስሊም ቡድኖች አፍሪካ ውስጥ ባሉ ክርስቲያኖች ላይ በድብቅ ጦርነት አፋፍመዋል የሚለውን ዜና ለንባብ አብቅቷል። አክራሪ ሙስሊሞቹ እጅግ ጥብቅ የሆነውን አይነት የሻሪያ ሕግ በብዙ አገሮች ላይ ለመተግበር በሚያደርጉት ከፍተኛ መረባረብ በ2012 ብቻ ብዙ ጥቃቶችን በተለያዩ ቦታዎች አድርሰዋል።
በእስልምና የበላይነት የሚያምነው የናይጄሪያው ቦኮ ሃራም (Boko Haram) የተባለው አክራሪ የእስላም እጅግ ቡድን ብዙ ጥቃቶችን ሰንዝሮአል። በጥር ወር በሁለት ቀናት ውስጥ 29 ክርስቲያኖች ጎምቤ (Gombe) ናይጄሪያ ውስጥ ተገድለዋል። ከወር በኋላ በቤተክርስቲያን በአምልኮ እንዳሉ በአጥፍተህ ጥፋ ግለሰብ ሶስት ክርስቲያኖች ተገድለዋል። በሰኔ ወር ቦኮ ሃራም ብዙ ቤተክርስቲያኖችን በቦንብ ሲያፈነዳ በክርስትያኖችና በሙስሊሙ መካከል ውጥረትን አነሳስቶአል። ቦኮ ሃራም ባወጣው መግለጫው ላይ «ሰላም ከፈለጋችሁ ክርስቲያን ሁሉ ወደ እስልምና መቀየር አለባቸው» ብሎአል።
እንዲሁም በታንዛኒያም ዩአምሾ (Uamsho) በተባለው አክራሪ የእስላም ቡድን ምክንያት የሃይማኖት ብጥብጥ ተከስቶአል። በግንቦት ዛንዚባር (Zanzibar) በተባለው ደሴት የሚገኙ ሶስት ቤተክርትያኖችን የዩአምሾ ቡድን አባላት አውድመዋቸዋል። በክልሉ ያለ አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ የዩአምሾ ጥቃት ድፍረት የተሞላው ነው ብሎ ያምናል «ከዚህ በፊት መንደር ውስጥ የሚገኝን ቤተክርስቲን ነበር የሚያጠቁት አሁን ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ሙስሊሞች በዛኑዚባር ከተማ ቤተክርስቲን አወደሙ» ሲል ተናግሮአል።
በኬንያም የእስልምና ፅንፈኝነት አለ በተለይም አልሻባብ (al-Shabaab) በተባለው አክራሪ የእስላም ቡድን አማካኝነት። በመጋቢት ከቤት ውጭ ይደረግ በነበረው የአምልኮ ስርአት ላይ በተወረወረ የእጅ ቦንብ ምክንያት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ከ30 በላይ የሚሆኑ ክርስቲያኖች ቆስለዋል። በሐምሌ ወር ሌሎች ሁለት ተጨማሪ ቤተክርስቲያኖች ጥቃት ደርሶባቸዋል። እነዚህ ሁሉ ጥቃቶች በአልሻባብ የተፈጸሙና የ17 ክርስቲያኖችን ሕይወት ያጠፉ ናቸው።
በብዙዎቹ ግድያዎች ላይ የመንግስት ባለስልጣኖች ክርስቲያኖችን ከጥቃት ለመከላከል አልቻሉም ወይም ይህንን የሚያደርጉትን አክራሪዎች ለመቅጣት የወሰዱት እርምጃ የለም። የእስልምና ፅንፈኝነት የተመሰረተው ሁሉም ሰው እስልምናን እንዲቀበልና እንዲሁም በእያንዳንዱ አገር ውስጥ የሻሪያ ሕግ ተግባራዊ ሆኖ ከማየት ከመነጨ ፍላጎት ነው። ጥቃቱ እየጨመረ ሲሄድ፤ መንግስታት ጉዳተኞችን ከጥቃት መከላከል ካልቻሉ ክርስቲያኖች አምላካቸውን በነፃነት የማምለካቸው ጉዳይ በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ትዝታ ብቻ ሆኖ ይቀራል።
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ