ቁርአንና ሳይንሳዊ ተዓምሮቹ
ጨረቃም የማይደረስባት ሆና ትቀራለች
የእስልምና ዳዋ ተዓምር እንዴት እራሱን እንደሚያፈርስ
በJochen Katz
ትርጉምና ቅንብ በአዘጋጁ
የሰው ልጅ ወደ ጨረቃ አድርጎት የነበረውን የሙስሊሞች ቁርአን በትንቢት ቀድሞ እንደተናገረው እጅግ ብዙ የሙስሊም ፕሮፓጋንዲሰቶች ይናገራሉ፣ ለዚህም ሐሳብ ደጋፊ የሆኑ እጅግ ብዙ አንቀፆችን ያመጣሉ፡፡ ይህንን በተመለከተ “የማሱድ ማሲሂየንን” Islamic humor reaching for the moon የሚለውን አስደናቂ ጽሑፍ እንድታነቡ በጣም አበረታታለሁ፤ ይህንን በተመለከተ “በሐሩን ያህያ” የተሰጠውን ሐሳብ አጠቃላይ በሆነ መልኩ መርምሮታልና፡፡
በዚህ በያዝነው አንቀፅ ውስጥ እኔ የምመረምረው “በካነር ታስላማን” ትርጉም መሰረት የቀረበውን ተመሳሳይ ነገር ነው እናም በአንዳንድ ልዩ በሆኑ ዝርዝሮች ላይ አስተያየትን እሰጣለሁ እንዲሁም “በማሱድ ማሲሂየን” ያልተዳሰሱ ጥቂት ጠቃሚ ነጥቦችንም እጨምራለሁ፡፡
ስለዚህም በታስላማን ስብከት የተሰጠውን አንቀፅ በአንቀፅ እስኪ እንሂድበት፡
የመጽሐፉ ምዕራፍ 16: ወደ ጨረቃ ጉዞ
ቁርአን 84 (የመቀደድ ምዕራፍ) ቁጥር 18 “በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)” ቁጥር 19 “ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለወጣላችሁ፡፡” ቁጥር 20 “የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?” ይላል፡፡
“ጨረቃ በአዕምሮአችን ውስጥ ውብ የሆኑ ቦታዎችና አስደሳች የምድር ቦታዎች የተያያዘ ነው፡፡ የጨረቃ ቀን አቆጣጠርን ለሚጠቀሙት እርሱ ትክክል የሆነ ካልኩሌተር ነው፡፡ የባህር ሞገድ መምጣትና መሄድ እንዲሁም የሚያስከትላቸው ነገሮች ለሰው ልጆች ሁል ጊዜ ምስጢር እንደሆነ ነው፡፡ ጨረቃ የሂሳብ ስሌትን አስትሮኖሚንና ደስተኝነትን ለማመልከት ሁልጊዜ ጥቅም ላይ ውላለች፡፡ በታሪክ ሁሉ ውስጥ ጨረቃ ሁልጊዜ የማይገኝ ነገር ምሳሌ ሆና ኖራለች፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በነቢዩ ጊዜ የነበሩ ናቸው፡፡”
ቋንቋውን በተመለከተ ከዚህ በላይ ያለው አንቀፅ ውብ በሆነ መንገድ ተቀናብሯል፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ ውስጥ ማናቸውም ወደ ጨረቃ ስለተደረገ ጉዞ በቁርአን ውስጥ አለ ስለሚባለው ትንቢት የሚሰጡት ምንም ጠቀሜታ የላቸውም፡፡ እንዲሁም ሁለተኛው አረፍተ ነገርማ ሳይንሳዊ ትርጉመ ቢስ ነው፡፡ በጨረቃ ቀን አቆጣጠር ውስጥ ጨረቃ የማገናዘቢያ ነጥብ ናት፡፡ ታስላማን ሊነግረን የሚፈልገው ነገር ጨረቃ እራሷ ቀን ትቆጥራለች በማለት ነውን? ከዚህም በላይ ደግሞ የእስልምናው የጨረቃ ካላንደር አንዱ ችግር ቀናትን በትክክል ለመቁጠር የማይቻል በመሆኑም ላይ ነው፤ ምክንያቱም አቋሙ ላይ ብቻ ሳይሆን በጨረቃ መታየትና አለመታየት ላይ የተመሰረተ በመሆኑም ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ የእስላማዊ ካሌንደርን የሚሰጡ ብዙ ድረገፆች ይህንን በተመለከተ ጥንቃቄዎችን ጨምረውባቸዋል፡፡
የሚከተሉት ሦስት አንቀፆች የታስላማንን መከራከሪያዎች ይዘዋል፡-
‘ለ1400 ዓመታት ከዚህ በላይ ያሉት እነዚህ ጥቅሶች ሳይገለጡ ቆይተው ነበር፡፡ በቁርአን ውስጥ “እና” ማለትም (ዋ) የሚለው አገናኝ የሚያገለግለው ነጥብን ለማጠንከር ነው፣ አንዳንድ ጊዜ እርሱ በእንግሊዝኛ መስተዋድድ “በ” ተገልጧል ይህም ጠንካራ ቃል ኪዳንን፣ ወይንም መሐላን ወይንም አንድ ሰውን ለምስክርነት ሲጣራና ሲሰጥ ነው፡፡ ተንታኞች “ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለወጣላችሁ፡፡” የሚለውን ቃል በተለየ መልክ አይተውታል፣ ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ጨረቃ ሊደረስባት የማትቻል ስለነበረች ነው፡፡ ወደ ጨረቃ መጓዝ ከአዕምሮ በላይ (ከግምት ሁሉ በላይ) የነበረ ነገር ነበርና፡፡”
“ይህ ከደረጃ ወደ ደረጃ ትጋልባላቸሁ ወይንም በአማርኛው ቁርአን መሰረት “ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለወጣላችሁ፡፡” ከአንድ መንፈሳዊ መውጣት (ማረግ) ጋር የተያያዘ ነበር ሲሆን፣ የሚያመለክተውም ከዚህ ዓለም ወደ ሌላው ዓለም የሚደረገውን መተላለፍ ነው፣ የአንድ ሰውን ከፅንስ ወደ ጎልማሳነት እንዲሁም ወደ እርጅና የሚደረገውን የዕድገት ደረጃ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ጥቅሶች የሚያዩት የሰው ልጆች ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ ገና አሁን ወዳልሆነ ትንቢታዊ ጊዜ ማለትም (የወደ ፊት) እንደሚያልፉ ነው፡፡ መንፈሳዊ ማረጎችና የሰው የአካላዊ ዕድገቶች ምንም አዲስ ነገሮች አይደሉም፡፡ ስለዚህም የጥንቶቹ እነዚህ አስተያየቶችና ትርጉሞች እውነታውን ያንፀባርቃሉ ብዬ አሁን አልልም፡፡ የጥቅሱ አውድ እንደሚያመለክተው ወደ ፊት አንድ የሆነ (የተለየ) ክስተት እንደሚጠበቅ (ሊሆን እንደሚችል) ያሳያል፡፡ የአረቢኛው “ታባክ” የሚለው “ደረጃ” በአማርኛው “ኹነታ” ተብሎ የተተረጎመው በቁርአን 67.3 ላይና በቁርአን 71.15 ላይ ተጠቅሷል፡፡ እነርሱም የሚያመለክቱት ለመንፈሳዊ ነገር ሳይሆን ተጨባጭ ለሆነ ነገር ነው፡፡ “መጋለብ” በአማርኛው “ትለወጣላችሁ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ጥቅም በርግጥ የሚያሳየው ጉዞን ነው፡፡ (የእንግሊዝኛው “riding from stage to stage” በትክክል ቢተረጎም “ከደረጃ ወደ ደረጃ ትጋልባላችሁ” የሚል ሐሳብ ያለው ቢሆንም በአማርኛው የተተረጎመው በተለየ መልኩ ነው፡፡ ((ይህ የአዘጋጁ አስተያየት ነው)) )
ቁጥር 19ን በዚህ መንገድ ከገለጥን በኋላ የኛ ትኩረት መምጣት ያለበት በቁጠር 18 ላይ በተጠቀሰው በጨረቃ ሐሳብ ላይ ነው ይህም ከደረጃ ወደ ደረጃ ትጋልባላችሁ የሚለው ከምድር ወደ ጨረቃ የሚደረገው ጉዞ በሮኬቶች የመሆኑን ሐሳብ ይደግፋል፡፡”
ታስላማን እንደገና እራሱን የሚያረጋግጠው የቁርአንን አንቀፆች እንደፈለገው መጠቀም የሚችል ባለሙያ አድርጎ ነው፡፡ “ዋ” ማለትም “እና” የሚለው ቃል አገናኝ ነው ምክንያቱም በፊት የመጣውን ቃል ከዚያ ቀጥሎ ከሚመጣው ቃል ጋር ያገናኛልና፡፡ ነገር ግን ከበፊቱ በኋላ የሚመጣውን አያጠናክርም ወይንም ትኩረት እንዲደረግበት አያደርግም፣ “ዋ” አንድ ነገርን የሚያጠናክር ቢሆን ኖሮ ማድረግ ያለበት ለአንባቢው ከተጠቀሰው ቃል ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ በመጠቆም ወይንም በመናገር ነበር እንጂ በአረፍተ ነገሩ አጋማሽ ላይ ይህንን አይጀምርም ቀድሞውኑ አረፍተ ነገሩ ምንም ለማለት እንደታቀደ ካልገባው በስተቀር፡፡ (ወይንም አረፍተ ነገሩ ምን እንደሚል አልገባውም ማለት ነው፡፡)
ስለዚህም አሁን እኛ “ዋ” የሚለውን ቃል የምር አድርገን እንመልከተው ስለዚህም ከአረፍተነገሩ መጀመሪያ ጀምሮ መጥቀስ እንጀምር፡ ማለትም ከቁጥር 16፡፡ (አትሳቱ በውጋገኑ እምላለሁ ቁጥር 16፣
- በሌሊቱም በሰበሰበውም ሁሉ (17)፣
- በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ) 18
- ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለወጣላችሁ፡፡ ቁጥር 19
- የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው? ቁጥር 20፣
- በነሱም ላይ ቁርአን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት ምን አላቸው? ቁጥር 21)፡፡
በትክክል “ዋ” ማለትም “እና” አይደለም “በ” ተብሎ የተተረጎመው፣ ነገር ግን መስተዋድዱ “በ” ማለትም በቁጥር 16 ላይ ያለው ነው ከቁጥር 16-18 ያሉትን ስሞችንና ገለጣዎችን ሁሉ የሚገዛውና የሚያሽከረክረው እርሱ ነው፣ እርሱም የእነዚያን የመሐላ ቃላት ሙሉ ዝርዝር ይሰጣል፡፡ ጨረቃ በዚያ የመሐላ ዝርዝር 16-18 ቀመር ውስጥ አንደኛዋ ብቻ ናት፡፡
ይህንን በትንሽ ታሪክ እናብራራው፡፡ ካንከር ታሰላማን ስሙ ሜሱት የተባለ ጓደኛ አለው ብላችሁ በአእምሮአችሁ አስቡ፤ እርሱም ለረጅም ጊዜ እንደሚጎበኘው ቃል ገብቶለታል ነገር ግን ጉብኝቱ እንደምንም ተፈፀመ፡፡ ሜሱት መኪና የለውም ስለዚህም አውቶቡስ መያዝ አለበት እንዲያውም አውቶቡሶችን ብዙ ጊዜ መቀያየር አለበት፡፡ ካንከር ሜሱትን በስልክ ጠርቶ የሚከተለውን ቃል ገባለት ‹በጨረቃ እምላለሁ የሚቀጥለው ሳምንት ከአውቶቡስ ማረፊያ ወደ አውቶቡስ ማረፊያ እነዳለሁ” አለው፡፡ ስለዚህ ካንከር ታስላማን በጨረቃ ላይ ነው የሚኖረው በማለት ልንገምት እንችላለን እንዴ? እንዲሁም በቱርክ ውስጥ አንድ ሰው ወደ ጨረቃ ለመሄድ አውቶቡስ መያዝ አለበትን?” ወይንስ በእስታንቡል ከተማ ውስጥ ያለው የሕዝብ መጓጓዣ መንገድ ስሙ “ጨረቃ” የሆነ የአውቶቡስ ማቆሚያ አለውን? የታስላማን ቤት አጠገብ የሆነ የአውቶቡስ ማቆሚያ አለውን?
ያ ምናልባትም የማይረባ ትርጉም ሊሆን ይችላል ነገር ግን ቁርአን 84ን ስናነብ ከአንቀፆቹ ላይ ታስላማን እንድናምን የሚፈልገው ያንን ነገር ነው፡፡
ከመሐላው የምስክርነት ፎርሙላ ክፍል ውስጥ የጨረቃን ጉዳይ ነጥሎ በማውጣት ከሚቀጥለውና የይዘቱን አረፍተ ነገር ከሚይዘው ሐረግ ጋር በማያያዝ ታስላማን የቁርአንን ክፍል ገንጥሎ አውጥቶ እንደገና በማዋቀር በክፍሉ ውስጥ የሌለውን ትርጉም በክፍሉ ውስጥ እያሰረፀ ነው፡፡ ታስላማን የመሐላን አወቃቀር የማያውቅና በእውነት በከፊል የተማረ ሰው ነውን? የሆነው ሆኖ የመሐላ ትርጉም በዊኬፒዲያ ውስጥ እንደሚከተለው ይነበባል፡-
መሐላ የእውነታ አረፍተ ነገር ወይንም ቃልኪዳን ነው፡፡ እርሱም አንድ ነገርን ወይንም አንድ መሐላ አድራጊ ሰው፤ የሚጠራው ቅዱስ አድርጎ የሚቆጥረውን ነገር፤ ብዙውንም ጊዜ እግዚአብሔርን ነው፡፡ ይህም ለቃልኪዳኑ ወይንም ለእውነቱ አረፍተ ነገር እንደምስክር አድርጎ ይጠራዋል፡፡ መማል ማለትም መሐላ መውሰድን ወይንም የከበረ ቃል ኪዳን መግባት ማለት ነው፡፡ (Wikipedia, Oath; accessed 17 October 2011)፡፡
በሌላ አነጋገር መሐላ ሁለት ክፍሎችን የያዘ ነው፡ 1. ምስክርን የሚጠራ (አንድ ወይንም ሁለት፣ አንድ ሰው ወይንም በቁርአን በኩል ደግሞ አንድ ነገርን የሚጠራው ክፍል) እንዲሁም፤ 2. የአረፍተ ነገሩን ይዘት (እውነታውን ወይንም የተስፋ ቃል ኪዳኑን ክፍል ነው)፡፡ በእኛ በኩል በቁርአን 84 ቁጥር 16-18 ያሉት የሚጣሩ ናቸው፣ ለምስክር የቀረቡ ጥሪዎች ናቸው ቁጥር 19 ደግሞ ይዘቱን ያቀርብልናል ይህም “በ-እምላለሁ ...” ቃል ኪዳን መሰረት ቀዳሚ የማረጋገጫ አረፍተ ነገር መሰረት ማረጋገጫ የተሰጠው ነው፡፡ ጨረቃ ደግሞ የተሰጠችው በዚህ ቃል መሰረት ምስክር እንድትሆን ነው ነገር ግን በምንም ዓይነት መንገድ ከዓረፍተ ነገሩ ይዘት ጋር ምንም ዓይነት ነገርን እንዲሰራ አይደለም፡፡ እነዚህን ሁለት የመሐላ ክፍሎች አንድ ላይ ማደባለቅ ማለት እራስን እንዳልተማረና እንደ መሐይም ማጋለጥ ማለት ወይንም ደግሞ የአንድ ኣረፍተ ነገርን ክፍል ሆነ ብሎ እንደሚያጣምምና እንደሚያበላሽ ሰው ማቅረብ ነው፡፡ እንደዚሁም አንቀፁ የቁርአን ክፍል ከሆነ በእርግጥ ከሆነ ደግሞ ይህ የሚሆነው አደገኛ ነገር ነው፡፡
ታስላማን ከዚያም በመቀጥል የራሱን የተበላሸ ሃሳብ ለማስረፅ እጅግ በጣም ብዙ ቃላትን ተጠቅሟል፡
“ተንታኞች “ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ” የሚለውን በተለያየ መንገድ ነው ያዩት፡፡ ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ጨረቃ የማትደረስ የነበረች በመሆኗ ነበር፡፡ ወደ ጨረቃ መሄድ ከግምት በጣም የራቀ ነበር፡፡
እኔ እንደማስበው የዚህ የጥንት ትርጉም ሐሳብ እውነታን አያንፀባርቅም ምክንያቱም (በአማርኛው ትለዋወጣላችሁ በአረብኛው ትጋልባላችሁ) በግልፅ የሚያሳየው ጉዞን ነውና፡፡” ብሏል፡፡
ይህንን ካለ በኋላ ቁጥር 19 እንደሚከተለው አስቀምጦታል፡ “የኛ ትኩረት የተሳበበት ነገር በቁጥር 18 ላይ ያለችው ጨረቃ ናት፤ እርሷም “ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ” የሚለውን ሐሳብ ትደግፋለች፤ ይህም በመንኮራኩሮች አማካኝነት ከምድር ወደ ጨረቃ የተደረገውን ጉዞ ነው፡፡”
ለማንኛውም የቁርአን 84 ቁጥር 19 የሚለውን ጥቂት ቆየት ብለን እንመለከታለን፤ ነገር ግን እኛ እንዳየነው ታስላማን እጅግ ብዙ የሆኑ የቋንቋ ስህተቶችን ፈፅሟል፣ ይህም የእርሱን ድንቁርና እና ወይንም እርሱ ለሚፈልገው ዓላማ ሊጠቀምበት ክፍሉን ሆነ ብሎ እንዳጣመመ ያሳያል፡፡
የመጀመሪያውም ስህተት እዚህ ላይ የምናየው እርሱ የክፍሉን አንቀፅ መዋቅር እንዳለ ማጥፋቱ ነው፡፡ ይህም ጥቁሱን ሲወስድ ከጥቅሱ መካከል ላይ በመጀመር ነው፣ ይህም የአረፍተ ነገሩን ጅማሬ በመደበቅ አንባቢዎች ግልጥ በሆነ መንገድ የመሐላውን መዋቅራዊ አቀራረብ እንዳያዩት በማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ስህተት ደግሞ እርሱ ከመሐላው ምስክር ክፍል ጨረቃን ማስወገዱና ከዋናው የይዘቱ ክፍል ጋር ማያያዙ ነው ይህ ደግሞ ተቀባይነት የሌለው የስህተት አጠቃቀም ነው፡፡
ከዚህ የትርጉም አቀራረብ ጋር የማፊዮሲ መሐላ ይመሳላል እርሱም እንዲህ ማለ፡ “በአባቴ ይህንን ሰው እገድለዋለሁ” ይህ ስለ ተቀናቃኞቹ አንዱ ወይንም የአደንዛዥ እፅ ንግዱን ለማገድ ስለመጣ የፖሊስ መርማሪ የተናገረውን ይመለከታል ታዲያ ይህ ማለት የእርሱ አባት የድርጊቱ ተቀባይ ማለት ነውን ማለትም እርሱ የራሱን አባት ለመግደል እየዛተ ነውን፡፡ ታስላማን የእርሱን አተረጓጎም ስህተትነት ለመገንዘብ እምቢተኛ ቢሆንም፤ ስህተቱን ባያርምም እንኳን እንዲሁም ነገር ግን ተመሳሳይን ነገር አሁንም ማሰራጨቱን ቢቀጥልም እርግጠኛ የምንሆነው ብዙዎቹ የእርሱ አንባቢዎች ይንን ችግር በአሁኑ ጊዜ እንደተረዱት ነው፡፡
ይህ ምልከታ ብቻ በብቃት የታስላማንን ትርጉም ይቃወመዋል እናም በዚህ ላይ ያለው ውይይት እዚህ ላይ ሊያበቃ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የሙስሊም አንባቢዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ምናልባት ባያምኑ በታስላማን የቁርአን ትርጉምና ትንተና ውስጥ ያሉትን ተጨማሪ ችግሮችንና ተቃርኖዎችን መመልከታችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡
(በታስላማን የተደረጉትን ብዙ ስህተቶች በእያንዳንዳቸው ውስጥ ገብተው ለመቆፈር የማይፈልጉ አንባቢዎች በቀጥታ ማለፍና የእርሱ ትርጉም በቁርአን የስህተት ትንቢት ውስጥ ለምን እንደመጣ አልፈው ለማየት ይችላሉ)
ሦስተኛው የእርሱ የስህተት ማስረጃ ትርጉመ-ቢስ አረፍተ ነገር ነው፡
“በቁርአን ውስጥ የአገናኝ ቃል “እና” (ዋ) ብዙውን ጊዜ አንድ ነጥብን ለማጠንከር ያገለግላል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በእንግሊዝኛው “በ” ሆኖ ያገለግላል ይህም ጠንከር ያለ ቃል ኪዳንን ሲያደርግ ነው ይህም መሐላን ሲወስድ ወይንም አንድ ሰውን ለምስክርነት ሲጠራ ነው፡፡”
ስለ ቁርአን ትልቅ መጽሐፍን ለሚጽፍ ሰው፤ ማለትም የቁርአን ተንታኝ ለሆነ ሰው እንዲሁም ከቀደሙት ተንታኞች የበለጠ እውቀት አለኝ ለሚል ሰው እጀግ በጣም መሰረታዊ የሆነውን የቋንቋውን ሕግጋት አለማወቁ በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ እጅግ በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ ይህንን እርሱ የማያውቀው ከሆነ ግን እጅግ በጣም በአጠቃላይም መሐይም ነው ማለት ነው፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ እርሱ የቋንቋውን ሕግጋት የሚያውቅ ከሆነና የቃሎቹን ትርጉሞች በማጣመም ሊጠቀምባቸውና የአረፍተ ነገሮቹን አወቃቀር ሆነ ብሎ ለማጣመም ከፈለገ ደግሞ የሚሆነው ነገር ከቀደመው ይልቅ የከፋ ነው፡፡ ይህም በአደባባይ መጋለጥ ይገባዋል፤ ምክንያቱም የእርሱን ማታለልና ማወናበድ ለብዙ አንባቢዎችና ለሰፊ አዳማጭ አስፋፍቶታልና፡፡
“ዋ” ወይንም “እና” የሚለው ቃል በምንም ዓይነት መንገድ “በ” ሊሆን አይችልም በቁርአንም ውስጥ እንኳን አይደለም፡፡ በዚህም ጉዳይ ላይ እንኳን ወይንም ማንኛውም ሌላ ቅድመ ቃል መስተዋድዱ በሁለት ወይንም ከዚያ በላይ በሆኑ መግቢያዎች ላይ በቀላሉ ከ”በ” ውጭ ሆኗል፡፡ እኔ “የሚቀጥለው ዓመት ወደ ጀርመንና ወደ ስዊትዘርላድ እሄዳለሁ” ብዬ ብናገር ከዚያም አገናኙ “እና” የሚቀጥለው ወደ መስተዋድዱ (ፕሮፖዝሺኑ) “ወደ” ወደሚለው ማለትም ስዊዘርላድንም ወደ ማጠቃለል ይዘልቃል ነገር ግን “እና” “ወደ” ማለት ግን አይደለም “እና” “ወደ” አይልም፤ እንዲሁም በፍፁም “ወደ” ሊል አይችልም፡፡ ስለዚህም ታስላማን አረብኛውን “ዋ” የገለጠበት አገላለጥ በቀላሉ የማይሆን ነገር ነው፡፡
የቀደሙት የቁርአን ተንታኞች ቁርአን 84ቁጥር 19 በተመለከተ የተለየ አመለካከት ነበራቸው ብሎ ታስላማን ሲናገር ትክክል ነው፡፡ በዚህ አረፍተ ነገር ላይ ያለው ነገር፤ ቁርአን ብዙውን ጊዜ እንደሆነው ሁሉ ምንም ትርጉም የማይሰጥና ምስጢራዊ እንደሆነ እስማማለሁ፡፡ ይሁን እንጂ አንቀፁ ሙሉ በሙሉ ግልፅ አይደለም የሚለው እውነታ ግን እኛ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ልናደርገው እንችላለን ማለት አይደለም፡፡ የቀደሙት ተንታኞችም የተለያየ አመለካከት ነበራቸው የሚለውም እውነታ እራሱ እንኳን ክፍሉን ለማጣመም ማስረጃ ሊሆንልን በፍፁም አይችልም እና ወደ ጨረቃ የሚደረግ የጉዞ ትንቢት ነው ልንለውና የአረፍተ ነገሩን አወቃቀር በማጥፋት ለማጣመም የሚያስችለን በፍፁም ሊሆን አይችልም፡፡
ታስላማን ትክክል ቢሆን እንኳን እርሱ እራሱን ነው የኮነነው፡፡ ይህንንም ያደረገው የቀደሙትን ተንታኞች ሪፖርት በማቅረቡ ነው እርሱም የእነርሱን ገለጣ እንዳጠናው አምኖ ተናግሯል ስለዚህም ስለ ቃላት አጠቃቀም ስለ ሰዋስው እና በአንድ አንቀፅ ውስጥ ስለ አሉ የአረፍተ ነገሮች አወቃቀር አላውቅም በማለት ሊናገር አይችልም፡፡ እርሱም በአንቀፁ ላይ ያደረገው ማጣመም ከቅንነት የመነጨ ስህተት አይደለም፣ እንዲሁም እርሱ ከእነርሱ በተሻለ መንገድ ስላወቀ አይደለም፣ ነገር ግን እርሱ ትንተናዎቹን አገናዝቧል ክፍሉንም አጥንቶታል፡፡ ስለዚህም የእርሱ ቀጣዩ ስህተት መሆን የሚችለው ሆነ ተብሎ የተደረገ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
በቁጥር 19 ላይ ያለው አረፍተ ነገር ምንም እንኳን ምስጢራዊ ቢመስልም እኛ ስለ ነገሩ ምንም እርግጠኛ ልንሆን አንችልም ማለት ግን አይደለም (ስለማንኛውም ነገር)፡፡ ወይንም እርሱ እኛ የምንፈልገውን ይልልናል ማለትም አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ በጣም ጠጋ ያለ ምልከታ እናድርግ፡፡
- (አትሳቱ በውጋገኑ እምላለሁ ቁጥር 16፣
- በሌሊቱም በሰበሰበውም ሁሉ (17)፣
- በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ) 18
- ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለወጣላችሁ፡፡ ቁጥር 19
- የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው? ቁጥር 20፣
- በነሱም ላይ ቁርአን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት ምን አላቸው? ቁጥር 21)፡፡
ቁጥር 16-18 የመሐላው የምስክር ክፍል ናቸው፣ ቁጥር 19 የአፅንዖት አረፍተ ነገር ነው፣ ማለትም የመሐላው ይዘት ነው እንዲሁም ቁጥር 20-21 ከዚያ በኋላ የሚጠይቀው ጥያቄ አንዳንድ ሰዎች የመሐመድን መልእክት ማለትም ቁርአንን ለምን እንደማያምኑ ጥያቄን የሚያቀርብ ነው፡፡
የመጀመሪያዎቹን አዳማጮች በተመለከተ ይህ በጣም ግልጥ ነው የቁርአን ጸሐፊ በቁጥር 19 ላይ ለቀረበው አረፍተ ነገር ይጠብቅ የነበረው ነገር የእምነትንና የመታዘዝን ምላሽ እንደነበረ ግልፅ ነው፡፡ በቁጥር 20-21 ላይ ያሉት አረፍተ ነገሮች በአሁን ጊዜ የተቀመጡ መሆናቸውን አስተውሉ ይህም ምንም እንኳን ቁጥር 19 ለእኛ ምንም ግልፅ ባይሆንልንም ጭምር ነው፣ ነገር ግን ለመጀመሪያዎቹ አዳማጮች በትክክል ግልፅ ነው ተብሎ የተቀመጠ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በተሰጠው አረፍተ ነገር አማካኝነት ከእነርሱ ፈጣን የሆነ እምነትን መጠበቅ ምንም ትርጉም የማይሰጥ ነገር ነበር ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እኛ የአረፍተ ነገሩን ሙሉ አውድ ላይኖረን ይችላል ማለትም ቁጥር 19 ለመጀመሪያዉ አዳማጮች የሚለውን ለመረዳት ብቁ የሆነ ማስረጃ የለንም ማለት ነው፣ ነገር ግን በእነርሱ ጊዜ ትርጉም ሰጪ የነበረ መሆን አለበት ማለት ነው፡፡ ከ1400 ዓመታት በኋላ ወደ ጨረቃ የሚደረግ ጉዞ የትንቢት አረፍተ ነገር ግን አልነበረም፡፡ ይህ በመጀመሪያ የታቀደው ትርጉም በፍፁም ሊሆን አይችልም፡፡ ልክ ታስላማን እንዳለው ይህ ሊሆን የሚችለው “የማይገመት” ነገር ሆኖ ነው፡፡ ስለዚህም በዚያን ጊዜ ሰዎች በመሐመድ እንዲያምኑ የመጥሪያ ምክንያት ሊሆን አይችልም ነበር፡፡ ስለዚህም አረፍተ ነገሩ በመሐመድ ጊዜ የነበሩ ሰዎች በቀላሉ ሊስማሙበት የሚችሉትና እንደ እውነተኛ አረፍተ ነገር የሚቀበሉት ቃል መሆን ይገባው ነበር፤ ይህም ምንም እንኳን በታሰበው ውጤት ላይ ባይስማሙም እንኳን ነበር፣ ማለትም በመሐመድ መልእክት እነርሱም እራሳቸው እንዲያምኑና የእስልምናን እምነት እንዲቀበሉት (እንዲያቅፉት) ለታሰበው ውጤት፡፡
በእርግጥ ተውላጠ ስሞቹን በምንመለከትበት ጊዜ ታስላማን ሆኖ የምናገኘው የማሳሳት ዋና ወንጀለኛ ሆኖ ነው፡፡ ቁጥር 19 የሚሰራው ጠቅላላ አረፍተ ነገር ሆኖ ነው ስለ “እናንተ” ማለትም ለሁሉም አዳማጭ ነው ይናገር የነበረው፡፡ እናንተ ሁላችሁም “ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡” (ስለዚህም ምንም እንኳን ግልጥ ባይሆንም የልማዳዊውና “ከልጅነት ወደ አዋቂነት ከዚያም ወደ እርጅና እና ወደ ሚቀጥለው ሕይወት ትለወጣላችሁ” የሚለው አተረጓጎም ስሜት የሚሰጥ ነው)፡፡ ስለዚህም በዚህ ሕይወት ውስጥ እናንተ የዕድገት ደረጃ እንዳላችሁ ሁሉ ከዚህ በኋላ በሚመጣው ሕይወት ውስጥም ሌላ ደረጃ ሊኖር እንደሚችል መገመት ተፈጥሮአዊ አይሆንምን? ስለዚህም እናንተ ከሞት በኋላ ስላለ ሕይወት በምታስቡበት ጊዜ ስለ ትንሳኤና ስለ ፍርድ እናንተ እንዴት ማመንን ትቃወማላችሁ? (እንዴት አናምንም ትላላችሁ?) የእኔን መልእክት እንዴት ልትቃወሙት ትችላላችሁ ጤነኛ አመለካከት ውጭ ሆናችሁ ከቀረበላችሁ ማስረጃ ውጭ ሆናችሁ?
የዚህ “የዳዋ” ስብከት ውስጣዊ ሎጂክ ይህ ነው፡፡ ክፍሉ እራሱ እንደሚለው (ሁላችሁ) ከዚህ ሕይወት ወደሚቀጥለው ትሄዳላችሁ ነገር ግን ይህንን የምታምኑት አንዳንዶቻችሁ ብቻ ናችሁ፡፡ ሌሎች ደግሞ አሉ “እነርሱ” የማያምኑት ናቸው፡፡ ሙስሊሞች ይህንን መልእክት የሚያምኑት ናቸው ሙስሊም ያልሆኑት እነዚያ ይህንን መልእክት የማያምኑት ናቸው (ቁጥር 20) እንዲሁም አይሰግዱም (ቁጥር 21)፡፡ ስለዚህም በቁጥር 19 ላይ ያለው “እናንተ” ሁሉንም ሰዎች ነው የሚናገረው ነገር ግን “እነርሱ” የሚለው (ቁጥር 20-21) ላይ ያለው የማያምኑት ናቸው ስለዚህም በውጭ ያሉት ናቸው ስለዚህም እነርሱ በሦተኛ መደብ ብዙ ቁጥር ነው የተነገረላቸው፡፡
እንደገናም “እናንተ ከሁኔታ ወደ ሁኔታ ትለዋወጣላችሁ” እነርሱ ግን አያምኑም፡፡ ስለዚህም ይህ ትለወጣላችሁ የሚለው ቃል (በአማርኛው) የሚያመለክተው ለሁሉም ሰዎች እንጂ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ተወስኖ “የአርምስትሮንግን” ወደ ጨረቃ መጓዝ የሚያመለክት አይደለም፣ ነገር ግን ሁላችንም ስለምናደርገው ጉዞ የሚናገር ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ በአማኞችና በማያምኑት መካከል የተደረገው መከፋፈል በመሐመድ በራሱ ጊዜ የሆነው ነገር ነው እንጂ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የሆነ ነገር አይደለም፡፡
የታስላማንን ትርጉም ለማግኘት “እናንተ” እና “እነርሱ” የሚሉት ተውላጠ ስሞች መቀያየር አለባቸው፡፡ “እነርሱ” (ሩቅ ያሉ ሰዎች) ይለወጣሉ፣ ስለዚህም “እናንተ” እዚህ ያላችሁት ለምንድነው የማታምኑት? ታስላማን እንድናምን የሚፈልገው ነገር ቁጥር 19 የሚናገረው ለመጀመሪያዎቹ ሰሚዎች “እናንተ” አይደለም በማለት ነው ነገር ግን በሩቅ ዘመን ሩቅ ላሉ የተወሰኑ ሌሎች ሰዎችን ማለትም ወደ ጨረቃ የሚጓዙ ሰዎችን ማለቱ ነው፡፡ በዚህም በጣም ጥቂት ሰዎች ወደ ጨረቃ ባደረጉት ጉዞ መሰረትም (በአፖሎ 11 ውስጥ ሦስት ሰዎች) ቁርአን ሁላችንንም አሁን እንደሚከተለው በማለት ይጠይቀናል፡ “እናንተ ታዲያ የማታምኑት ለምንድነው?”
ወድ አንባቢዎች ሆይ ይሄ አይሆንም! እናንተ ጉዞ እንደወሰዳችሁ አስተውሉ፡፡ ማስተዋል ያለበትን አስተሳሰባችሁን አንቁት አዕምሮአችሁን ደግሞ ከተመረዘበት አንፁት፣ እነዚህ ዳዋጋኒዲስቶች (የዳዋ ሰባኪዎች) እና የቁርአን ጠምዛዦች እንዲያታልሏችሁና እንዲያወናብዷችሁ አትፍቀዱላቸው!
የቁርአን ጸሐፊ “አንድ ቀን የሆኑ ሰዎች ወደ ጨረቃ ይሄዳሉ” ለማለት አስቦ ቢሆን ኖሮ ይህንን ለመናገር ምንም የሚያግደው ነገር በፍፁም አልነበረበትም፡፡ ይህንን በግልጥ ለመናገር ያስችሉ የነበሩት ቃላት ሁሉም ነበሩለት፣ ለዚህም የሚያስፈልጉት ሁሉም ቃላት በቁርአን ውስጥ እንኳን ይገኛሉ፡፡ በመሐመድም ጊዜ ይህንን ለመግለጥ በፍፁም የማይቻል ነገር አልነበረም፡፡
ይሁን እንጂ እኛ ነገራችንን ገና አልጨረስንም፡፡
ታስላማን ይቀጥላል፡-
እነርሱ ለምን አያምኑም?
ጨረቃን ለመርገጥ የመጀመሪያው የተደረገው በራሺያ መንኮራኩር ሉና 2 ነበር (መስከረም 12 1959 እኤአ) ከዚያም ሉና 3 የጨረቃን የሩቅ ጎን ፎቶግራፍ ወሰደ፡፡ ነገር ግን እጅግ በጣም ጠቃሚው ክስተት በጨረቃ ላይ የተደረገው ማረፍ ነበር እርሱም በሐምሌ 21 1969 በኔል አርምስትሮንግ እና አብረውት በአፖሎ 11 ውስጥ በነበሩት በጓደኞቹ የተከናወነው ነበር፡፡ በድንግዝግዝ ቴሌቪዝን የሚታው የማረፍ ክስተት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም አስደናቂው እይታ ነበር፡፡ የማይቻል ተብሎ ይታሰብ የነበረው ነገር እውነት ሆነ፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ክስተት እንደ ሳይንሳዊ ግኝት የጠቆሙትና ሃይማኖትን ለመከራከር የተጠቀሙበት አዎንታዊዎች ግን ነበሩ፡፡ አንዳንድ ጠባብ የሆኑ (ዝቅተኛ አመለካከት ያላቸው) የእስላም ሊቃውንት እንዲህ ዓይነት ክስተት መከናወኑን ውሸት ነው በማለት ተከራክረውም ነበር፡፡ እናም ሰው በጨረቃ ላይ አረፈ በማለት የሚናገር ማንም ሰው ቢኖር የተረገመ ይሁን ብለው ነበር፡፡ (ቆይቶም) የተዓምራዊ ትንቢቱ ወደ እውነት መጣ የእግዚአብሔርን ጥበብና ኃይል እንደገና ለማሳየት፡፡
ከቁጥር 18ና 19 ቀጥሎ የሚመጣው ቁጥር 20 ወደ ጨረቃ የሚደረግ ጉዞ ትንቢት የተነገረባቸው እና “ስለዚህም እነርሱ ለምን አያምኑም?” የሚለው ሊጠቁም የሚችለው ለማያምኑትና ለእግዚአብሔር አስደናቂ ጥበብ እውራን ለሆኑት ነው፣ ይህን ሳይንስ በሃይማኖት ላይ ያገኘው ድል ነው በማለት ለሚቆጥሩት ነው፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሱት በሙሉ ጥቅመ ቢሶች ናቸው፡፡ እነርሱ በሙሉ የተቃውሞ መልስ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ የቁርአን ክፍል ውስጥ ወደ ጨረቃ የሚደረግ ጉዞን በተመለከተ ምንም ትንቢት የለም፡፡ እነርሱም የሚናገሩት እኔ እነዚህን ክፍሎች ለመጥቀስ እፈልጋለሁ “ሊያመለክቱ ይችላሉ” የሚሉትን ቃላት ብቻ ነው፡፡ ታስላማን በመጨረሻ ያመነው ነገር የእርሱ ትርጉም ትክክል ስለመሆኑ እርግጠኛ ሊሆን እንደማይችል ነው፡፡
ከዚህም በላይ ከታስላማን ትኩረት ያመለጠ አንድ የመጨረሻ ነገር፤ ግን እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ዝርዝር አለ፡፡ ምንም እንኳን አሁንም እኔ የሞተ ፈረስን እየመታሁ ቢሆንም ከዚህ ቀጥሎ ነው የመጨረሻው ምት የሚመጣው፡፡
የሐሰት ትንቢት?
“በቁርአን 84 ቁጥር 18 ላይ ያለው ጥቅስ “ጨረቃን” በቀላሉ አይጠቁምም ነገር ግን ስለ ጨረቃ የተወሰነ የዙረት ወቅት ነው የሚያሳየው፡፡” የታስላማን የምዕራፉ የመጀመሪያው መስመር የሚናገረው፡
“ጨረቃም ሙሉ በሆነችበት ጊዜ” ቁጥር 18፡፡
ታስላማን ከቁጥር 18 ላይ ወደ ቁጥር 19 “ጨረቃ” የሚለውን ብቻ ለምን ወሰደ፣ ለምን በቁጥር 18 ላይ ስለተነገረለት “ምን ዓይነት ጨረቃ” ለሚለው ለምን ትኩረትን አልሰጠም? ይህንን የግዴለሽነት መዝለል እናስተካክለው፡፡
ታስላማን በግልፅ የዚህን የቁርአንን ትንቢት ያያዘው በአጠቃላይ ወደ ጨረቃ ከተደረጉት ተልእኮዎች ጋር አይደለም ነገር ግን ወደ ጨረቃ ከተደረገ አንድ የተለየ ጉዞ ጋር ነው፣ እርሱም ሲጽፍ፡
“ነገር ግን እጀግ በጣም ጠቃሚው ክስተት በጨረቃ ላይ የተደረገው የሰው ልጅ ማረፍ ነው፡፡ በአፖሎ 11 ውስጥ በነበሩት በኒል አርምስትሮንግና በጓደኞቹ በሐምሌ 21 1969፡፡”
ስለዚህም ለጥቄው መልስን እንፈልግ፡፡ በዚህ የአፖሎ 11 ጉዞ ወቅት የጨረቃ ሁኔታ ምን ይመስል ነበር?
የሚያስደስተው ነገር ኢንተርኔቶች በአሁኑ ጊዜ ሙሉ የሆነ መጠቀሚያን ይሰጡናል ይህም የጨረቃን ሁኔታ መቀመር የምንችልበት ነው፡፡ የሚፈቅድልንም የጨረቃን ሁኔታ በማንኛውም ዘመንና አገር እንዲሁም ጊዜ ልንፈልግ እንድንችል በማድረግ ነው፡፡ የ1969 ዓ.ም መርጠን ለንደንን ከተማ ብናደርግ ዓለም አቀፍ ሰዓት በግሪኒች ፕራይም መሪዲየን ስላለ የሚከተለውን ሰንጠረዥ ማግኘት እንችላለን፡፡
የጨረቃ ዘመን | አዲስ ጨረቃ | 1ኛ ሩብ | ሙሉ ጨረቃ | 3ኛ ሩብ | ጊዜ |
---|---|---|---|---|---|
576 | 14 ሐምሌ 15.12 | ሐምሌ 22፤13.10 | ሐምሌ 29፤03.45 | ነሐሴ 5፤02.39 | 29 ቀን ከ 15.05 ሰዓት |
አፖሎ 11 ሐምሌ 16 (13.32.00UT) ተተኩሳ በጨረቃ ላይ ያረፈችው ሐምሌ 20 (20.17.40UT)፤ ከዚያም ከጨረቃ ላይ የተነሳችው ሐምሌ 21 (17.54.01UT) እናም በምድር ላይ ተመልሳ ያረፈችው ሐምሌ 24 (16.50.35UT) የነበረ መሆኑን ስንመለከት ግልጥ የሚሆነው “ወደ ጨረቃ ጉዞ” የሚለው (የታስላማን ርዕስ) በአጠቃላይ ተከናውኖ የነበረው ጨረቃ ከምድር ስትታይ ከግማሽ በታች ሆና ነበር ማለት ነው፡፡ በእርግጥ ግን አፖሎ 11 ጨረቃን ለቃ ወደ ምድር ባደረገችው ጉዞ ጨረቃ ከምድር ስትታይ ገና ከግማሽ ጨረቃ በታች ሆና ነበር፡፡
በሌላ አነጋገር የታስላማንን የክፍሉን ትርጉም (የውሸትና የመጠቀሚያ ማድረጉን) ከተቀበልነው የምናገኘው ነገር የሚሆነው እጅግ በጣም ግልጥ የሆነ የውሸት ትንቢት ያለበት ቁርአን ይሆናል፡፡ (ማለትም ቁርአንን የሚያደርገው እጅግ በጣም የውሸት ትንቢት ያለበት መጽሐፍ ነው)፡፡ ኔል አርምስትሮንግ አፖሎ 11 ላይ ወጣ እንጅ “ከኹነታ ወደ ኹነታ አልተለዋወጠም” ወደ ጨረቃ፤ ጨረቃ ሙሉ በነበረችበት ጊዜ ነገር ግን ጨረቃ ከግማሽ በታች ትታይ በነበረበት ጊዜ ነበር የተመለሰው፡፡ ስለዚህም በቁርአን ውስጥ ሳይንሳዊ ተዓምራትን በማስገባት ታስላማን እጅግ በጣምና በሁሉም አቅጣጫ ወድቋል፡፡
ጥቃቅን ነገሮች
ሌሎቹስ የጨረቃ ተልእኮዎች?
ሰዎች የነበሩባቸውን የጨረቃ ሌሎች ተልእኮዎችን ማግኘት በጣም ቀላል ነው፡፡ አፖሎ 11፣ 12፣ 13፣ 14፣ 15፣ 16፣ 17 እና ወደ ጨረቃ የሄዱበትንና የተመለሱበትን ቀናቶቻቸውን ከዚያም የጨረቃ ሁኔታዎችን (ግማሽ ሙሉ ወይንም ከሙሉ በታች) ማስላት ይቻላል፡፡
ተልዕኮ | የቆየበት ጊዜ | የሙሉ ጨረቃ ቀናት |
---|---|---|
አፖሎ 11 | 16-24 ሐምሌ 1969 | 29 ሐምሌ |
አፖሎ 12 | 14-24 ሕዳር 1969 | 29 ሐምሌ23 ሕዳር |
አፖሎ 13 | 11-17 ሚያዝያ 1970 | 21 ሚያዝያ |
አፖሎ 14 | 31 ጥር እስከ 9 የካቲት 1971 | 10 የካቲት |
አፖሎ 15 | 26 ሐምሌ እስከ 7 ነሐሴ 1971 | 6 ነሐሴ |
አፖሎ 16 | 16-27 ሚያዝያ 1972 | 28 ሚያዝያ |
አፖሎ 17 | 7-19 ታህሳስ 1972 | 20 ታህሳስ |
(ማስታዎሻ፡ ከቴክኒች ችግር የተነሳ አፖሎ 13 ላይ የነበረው ቡድን በጨረቃ ላይ አላረፉም ነገር ግን በጨረቃ ዙሪያ አንድ ጊዜ ከዞሩ በኋላ ወደ ምድር ተመልሰዋል) ማጠቃለያ፡ ከዚህ በላይ ያለው መረጃ እስላማዊ የፕሮፓጋንዳ አስተላላፊዎችን ለማሳፈር የተዘጋጀ ይመስላል፡፡ እግዚአብሔር የጨረቃን ተልዕኮዎች ከእነዚህ የጨረቃ ጉዞዎች መካከል አንዳቸውም እንኳን በሙሉ ጨረቃ ጊዜ የተደረጉ አልነበሩም እንዲሁም ደግሞ ወደ ምድር የተደረገውም በረራ እራሱ የተከናወነው ሙሉ ጨረቃ ከመሆኑ በፊት ነበር፡፡ በሁለቱ ተልእኮዎች ብቻ አፖሎ 12 እና 15 ብቻ ጠፈርተኞቹ ከኋላቸው ሙሉ ጨረቃን አይተዋል ይህም ወደ መሬት ከመመለሳቸው አንድ ቀን በፊት ነው እነርሱም የተጓዙት ከሁኔታ ወደ ሁኔታ ወደ መሬት ሲመለሱ ጨረቃ ሙሉ በሆነችበት ጊዜ ነበር፡፡
ሌሎቹስ መሐላዎችስ?
ለመሐላው የመጨረሻ ምስክር ጨረቃ ከሆነች በመጨረሻው የይዘቱ አረፍተ ነገር ውስጥ ከተደባለቀች ሌሎቹስ ሁለት ምስክሮች? በቁጥር 19 ላይ ያለው ጨረቃ ወደ መጨረሻ ቦታ ከተወሰደች ለጉዞው ከዚያም በእርግጥ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ጥቅሶችስ? ቁጥር 16-17 እንደሚከተለው ይላሉ፡
(አትሳቱ በውጋገኑ እምላለሁ ቁጥር 16፣ በሌሊቱም በሰበሰበውም ሁሉ (17)፣)
እነዚህ ሁለቱ ተጨማሪ የትንቢት መረጃዎችንም ይሰጡናል ሀ. ይህ ጉዞ የተጀመረው በጅማሬው ላይ ነው ለ. ጉዞው እራሱ የሚከናወነው በሌሊት ጊዜ ነው፡፡ ስለዚህም እኛ የምንጠይቀው፡ አፖሎ 11 ጉዞ የጀመረችው በስንት ሰዓት ነበር የሚለውን ነው፡፡ ከዚህ በፊት የተጠቀሰው የአፖሎ 11 የመረጃ ገፅ ይህንን መልስ ይሰጠናል፡ የተተኮሰችው፡ ሐምሌ 16 ቀን 1969 ከሰዓቱ 13.32.00 UT (09:32 a.m. EDT) ) Kennedy Space Center Launch Complex 39A፡፡ ስለዚህም እኛ እዚህ ላይ የቀኑን ሰዓት በተመለከተ የምናገኘው ጥንድ ተቃርኖ ነው፡፡ በሐምሌ ወር ከጠዋቱ 9.32 በፍሎሪዳ በጣም ብሩህ ቀን በምንም መልኩ ውጋጋን ውስጥ ሳይገባ ወይንም ሊመሽ ሳይል ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጅማሬው ሊመሽ ሲልም ማለትም ፀሐይ እየገባች ጨለማው ሲመጣ አልነበረም፣ ነገር ግን በጠዋት ነበር እናም ኦፖሎ 11 በቀኑ ውስጥ ነው የመጠቀችው እንጂ ወደ ጨለማውና በጨለማው ውስጥ አልነበረም፡፡
ከዚህ ቀጥሎ እኛ የምንጠይቀው፡ ማታ ማለት ለመሆኑ ምን ማለት ነው? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ አንድ ቦታ በጨለማ ውስጥ ነው ማለት በምድር ግርዶሽ ውስጥ ነው ያለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህም የፀሐይ ብርሃን ጨረር አይደርሰውም ማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ በውጭው ሕዋው ውስጥ ጨለማ ወይንም ሌሊት የሚባል ነገር አይኖርም ምክንያቱም ፀሐይን ሊሸፍኑ የሚችሉ ትልቅ የሆኑ ነገሮች ወይንም አካላት የሉምና፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ የአፖሎ 11 የጨረቃ መንኮራኩር በጨረቃ ላይ ያረፈችው ፀሐይ በወጣባት የጨረቃ ጎን ነበር ማለትም በጨረቃ የቀኑ ጎን በኩል ነበረች፡፡ በዚያም በጨረቃም ላይ እንኳን ጨለማ አልነበረም፡፡ የሚከተለውን ስዕል በጥንቃቄ ተመልከቱት፡
(Source: Wikipedia, Moon; 24 October 2011)
ወደ ጨረቃ የተደረገው የአፖሎ 11 ጉዞ በደማቅ የጨረቃ ወቅት ነበር፡፡ ተልእኮው የተጀመረው በምድር የቀን ሰዓት ሆኖ በጨረቃም ላይ የታረፈው በፀሐይ ብርሃን በኩል ባለው የጨረቃ ጎን ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ያለውን ስዕል ስንመለከት ግልፅ ሊሆን የሚገባው ነገር ማንኛውም በቀጥታ በረራ የነበረው በፀሐይ ብርሃን ሙሉ ብርሃን ውስጥ እንጂ በጭራሽ በምድርም ሆነ በጨረቃ ጥላ ውስጥ እንዳለነበረ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ያለው ስዕል በስኬል መጠን ግንዛቤ ያልተሳለ በመሆኑ በንፅፅር ሊያሳይ የሚችለውን ጉዞ ከዚህ በታች ባለው እንደሚከተለው እንመለከት፡፡
(Source: Apollo 11's Translunar Trajectory; 24 October 2011)
ፀሐይ በላይኛው ስዕል በጣም ርቃ በግርጌው ነው የምትታየው ወይንም በጎን እይታ ደግሞ በላይ ነው የምትታየው፡፡ ከጉዞው መንገድ ላይ እንደሚታየው ይህም እንደገና የምንገነዘበው ነገር አፖሎ 11 በተጓዘችት ወቅት በምንም መንገድ በጨለማ ውስጥ ልትሆን እንደማትችል ነበር፡፡ ለማጠቃለል ያህል አፖሎ 11 በብሩህ ፀሐይ ተነስታ ከምድር ሩቅ በሆነችበት ቅፅበት ውስጥ ከሚታው የጉዞ ቅርፅ ላይ ስንመለከት የምድርን ጥላ ማለፍ በጣም ትንሽ ነበር የሚሆነው፡፡ አፖሎ 11 መደ መሬት ተመለሰች፡ ሐምሌ 24፣ 1969 16:50:35 UT (12:50:35 p.m. EDT) ስለዚህም የመመለሻውም ጉዞ እንኳን በጨለማ አልነበረም፡፡
መደምደሚያ፡ ጉዞው በጠቅላላ የተከናወነው በብሩህ የቀን ብርሃን ወቅት ነበር፡፡ ስለዚህም በቁርአን 84.17 ላይ በሌሊቱም በሰበሰበውም ሁሉ (17) የሚለውን ለአፖሎ 11 የጨረቃ ጉዞ ጋር ማገናኘትና በጨለማ ተደረጎ ነበር የሚለው ትርጉም የሚመስለው (ሐሳቡ የተሳለው) በካነር ታስላማን አዕምሮ ውስጥ ብቻ እንደሆነ ነው፡፡
ለምን ክርስትያኖች?
ይህ ክስተት አንዳንድ የሙስሊም ፕሮፓጋንዲስቶች እንዲሆን ለማድረግ እንደሚፈልጉት ለሙስሞች በእርግጥ በጣም ወሳኝ ከሆነ፡፡ (ይህንን በተመለከተ Allah’s timing? ና Splitting the Moon በሚል ርዕስ የተጻፉትን ተመልከቱ)፡፡ እንዲሁም አንድ ብቻ ሳይሆን እጅግ ብዙ የሆኑ ቁርአናዊ ተዓምራታዊ ትንቢቶች ውስጥ የአፖሎ 11ን የጨረቃ ጉዞ ታሪካዊ ክስተት የሚናገሩ ሙስሊሞች እግዚአብሔር ይህንን አንድ ክስተት በብዙ መንገድና በተለያዩ ኮዶችና ዝርዝሮች በቁርአን ውስጥ በማስቀመጡ አይወናበዱምን? እንዲሁም ሙስሊም ያልሆኑትን (የማያምኑትን) ወደ ጨረቃ መላካቸውስ አያደናግጣቸውምን? ከእነርሱም መካከል ቢያንስ አንዱ እጅግ በጣም የተሰጠ ክርስትያን ነበር፤ ኤድዊን አልድሪን፣ እርሱም በጨረቃ ላይ እያለ የጌታ ኢየሱስን ስቅለትና ትንሳኤን የጌታን እራት በመውሰድ እዚያ ላይ ያከበረ ሰው ነበር፡፡
አሁንም ተጨማሪው ቀውስ!
በማንኛውም ዋና የሆነ የዓለም ታሪክ ውስጥ እንደምንም ተደርጎ የእስልምና ድል መገኘት አለበት፡፡ እንደምንም ተደርጎ እስላም ከእዚያ ውስጥ ዋናውን ምርት ማግኘትና አንዳንዱንም ክብር መውሰድ አለበት፡፡ ስለዚህም አንዳንድ ሙስሊሞች ኔል አርምስትሮንግ በጨረቃ ላይ እያለ “አደሃን” ሲደረግ ሰምቶ ወደ እስልምና እንደመጣ ተረትን ቢፈጥሩም አያስደንቀንም ይህንን በተመለከተ የሚቀጥለው ጊዜ “ኔል አርምስትሮንግ እንዴት ሙስሊም ሆነ?” የሚለውን ጽሑፍ ተመልከቱ፡፡
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡
ቁርአን ሰፊ ተቀባይነት እንዲያገኝ እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ የእስልምና ሰባኪዎች ብዙ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ በመሆኑም ከእያንዳንዱ የቁርአን ቁጥርና ሐሳብ ላይ ሳይንሳዊ ነው የሚሉትን ነገር ማቅረብንና ቁርአን የተነበየው ሳይንስ ነው ማለትን ተያይዘውታል፡፡ የሚገርመው ሳይንሳዊ በመባል የቀረቡት ሁሉ ከዚህ በላይ ፀሐፊው ጨረቃ ላይ ማረፍን አስመልክቶ እንዳቀረበው የትርጉም ጥምዘዛ የተደረገባቸውና ከእውነተኛ ሳይንስ የራቁ ናቸው፡፡
ቁርአን ሳይንሳዊ መረጃን ሊሰጥ የማይችል መሆኑን ከዚህ በላይ የቀረበው ብቻ ብቁ ቢሆንም፣ በተከታታይ በሙስሊሞች በዋናነት ስለሚጠቀሱት ሳይንስ የተባሉ ነገር ግን ያልሆኑ ነገሮችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡
ከዚህ በላይ የቀረበውን በጥሞና ላነበባችሁት ግን ማሳሰቢያ ሳንሰጣችሁ ልናልፍ አንፈልግም፡፡ ማሳሰቢያችንም በእውነት ዙሪያ ላይ የሚሽከረከር ነው፡፡ አንድ የሃይማኖት መጽሐፍ የሚናገራቸው ትንቢቶች ግልፅና የሚፈፀሙ ወይንም የተፈፀሙ የሚሆኑት ከምን የተነሳ ነው? የዚህን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችለን መንደርደሪያ ሐሳብ የሚመጣው ትንቢቱን የተናገረው ማነው? ከሚለው ጥያቄ ላይ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እጅግ በጣም ብዙ ትንቢቶች ተነግረዋል፣ ምንጫቸው እግዚአብሔር ሲሆን የተነገሩት ደግሞ እግዚአብሔርን በሚያውቁና እርሱም በላካቸው ሰዎች ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች አብዛኛዎቹ ተፈፅመዋል፣ አፈፃፀማቸውም ምንም እንከን በሌለበት ሁኔታ እንደሆነ ትንቢቶቹን ያጠኑ ሁሉ አረጋግጠዋል፡፡ ገና የሚፈፀሙም ትንቢቶች አሉ እነርሱም በትክክል ይፈፀማሉ፡፡ አንድ የተንቢት መጽሐፍ እንደሆነ የሚነገርለት መጽሐፍ በተደጋጋሚ ተሳስቶ ከተገኘ፣ አንባቢዎቹና ተከታዮቹ ጥያቄዎችን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ከየት የመጣ ነው ምንጩ ፈጣሪው እግዚአብሔር ነው ወይ? ለምን ተሳሳተ ስህተቱን ለማረምና እንዳልተሳሳተ መቁጠርና ማስቆጠር ትክክል ነው ወይ? የሚሉት ሁሉ መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡
አንባቢዎች መጽሐፍ ቅዱስን በማግኘት እንዲያነቡ እያበረታታን በጣም በትኩረት እንዲያስቡበት የሚያስፈልጋቸው ነገር የዘላለም ሕይወታቸው ጉዳይ መሆኑን ጭምር ነው፡፡ ኃጢአተኛው ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቀው እንዴት ነው? ለዚህ መሰረታዊ ጥያቄ መልስ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ስለዚህም ፈልጋችሁ አንብቡት ጌታ እግዚአብሔርም በፀጋውና በምህረቱ የዘላለምን ሕይወት መንገድ በቃሉ በኩል ይግለጥላችሁ አሜን፡፡
የትርጉም ምንጭ: And the Moon remains … out of reach How an Islamic dawah miracle self-destructs
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ